የጥናት እርዳታዎች
ሔዋን


ሔዋን

በዚህች ምድር ላይ የኖረች የመጀመሪያዋ ሴት (ዘፍጥ. ፪፥፳፩–፳፭፫፥፳)። የአዳም ባለቤት ነበረች። በዕብራውያን ቋንቋ የዚህ ስም ትርጉም “ህይወት” ነው። ስሟም የተሰጣት “የሕያዋን ሁሉ እናት” ስለነበረች ነው (ሙሴ ፬፥፳፮)። እርሷ እና የመጀመሪያው ሰው አዳም ለሰው ዘር ዘለአለማዊ እድገት ባደረጉት የዘለአለም ክብርን ይካፈላሉ።