የጥናት እርዳታዎች
ብሉይ ኪዳን


ብሉይ ኪዳን

በመንፈስ ቅዱስ ተፅዕኖ ስራ የሰሩ እና በብዙ መቶ አመታት ስለኢየሱስ ክርስቶስ እና ስለወደፊት አገልግሎቱ የመሰከሩ የጥንት ነቢያት ፅሁፎች ናቸው። ይህም የአብርሐምና የትውልዶቹን ታሪኮች፣ እናም ከአብርሐም ጀምሮ፣ ጌታ ከአብርሐምና ከትውልዶቹ ጋር ስለገባው ቃል ኪዳን፣ ወይም ምስክር፣ ታሪክ ይዘረዝራል።

የመጀመሪያው አምስት መፅሐፎች የተጻፉት በሙሴ ነበር። እነዚህም ኦሪት ዘፍጥረት፣ ኦሪት ዘፀአት፣ ኦሪት ዘሌዋውያን፣ ኦሪት ዘኁልቁ፣ ኦሪት ዘዳግም ነበሩ። ኦሪት ዘፍጥረት ስለምድር፣ ስለሰው ዘር፣ ስለቋንቋዎች፣ ስለዘሮች፣ እና ስለእስራኤል ቤት መጀመሪያ ስረ ነገር ይጠቅሳል።

የታሪክ መፅሐፎቹ ስለእስራኤል ድርጊቶች ይነግራሉ። እነዚህ መፅሐፎችም ኢያሱ፣ መሳፍንት፣ ሩት፣ ፩ እና ፪ ሙኤል፣ ፩ እና ፪ ነገስት፣ ፩ እና ፪ ዜና መዋዕል፣ ኤዝራ፣ ነሀምያ፣ እና አስቴር ናቸው።

የግጥም መፅሐፎች አንዳንድ የነቢያትን ጥበቦች እና ስነ ፅሑፎችን ይመዘግባሉ። እነዚህም ኢዮብ፣ መዝሙር፣ ምሳሌዎች፣ መክብብ፣ መኃልየ መኃልይ ዘሰለሞን፣ ሰቆቃወ ኤርምያስ ናቸው።

ነቢያት እስራኤልን ስለኃጢያቷ አስጠናቀቋት እናም ታዛዥ በመሆን ስለሚመጡት በረከቶችም መሰከሩ። እነርሱም ንስሀ ለሚገቡት፣ ስነስርዓቶችን ለሚቀበሉት፣ እና በወንጌሉ ለሚኖርት ኃጢያት ስለሚከፍለው ስለክርስቶስ መምጣት ተነበዩ። የነቢያቱ መፅሐፎችም፣ ኢሳይያስ፣ ኤርምያስ፣ ሕዝቅኤል፣ ዳንኤል፣ ሆሴዕ፣ ኢዩኤል፣ ዓሞጽ፣ አብድዩ፣ ዮናስ፣ ሚክያስ፣ ናሆም፣ እንባቆም፣ ሶፎንያስ፣ ሐጌ፣ ዘካርያስ፣ ሚልክያስ ነበሩ።

ብዙዎቹ የብሉይ ኪዳን መፅሐፎች የተጻፉት በእብራውያን ቋንቋ ነበር። አንዳንዶቹ ጽሁፎች አሬማውያን የሚባል የተመሳሰለ ቋንቋ የያዙ ናቸው።