የጥናት እርዳታዎች
የኪዳን ታቦት


የኪዳን ታቦት

ደግሞም የያህዌህ ታቦት እና የምስክር ታቦት ተብሎ የሚታወቀው የኪዳን ታቦት በወርቅ የተሸፈነ ከእንጨት የተሰራ የአራት ማዕዘን አይነት ሰንዱቅ ወይም ሳጥን ነበር። ከእስራኤላውያን የሀይማኖት ምልክቶች የጥንት እና ታላቅ ቅድስና ያለው ነበር። መደረቢያውን የሚሰራው የስርየት መክደኛው እንደ ያህዌህ የምድር መኖሪያ ቦታ ይታሰብበት ነበር (ዘፀአ. ፳፭፥፳፪)። ቤተመቅደሱ በተፈጸመበት ጊዜ፣ የኪዳን ታቦት፣ በአካል ከሁሉም በላይ ቅዱስ በሆነው ቦታ፣ በቅድስተ ቅዱሳን ውስጥ ተቀመጠ (፩ ነገሥ. ፰፥፩–፰)።