የህጻን ጥምቀት
ስምንት አመት ከሆነው ከተጠያቂነት እድሜ በታች የሆኑትን ህጻናትን እና ልጆችን አስፈላጊ ሳይሆን የመጥመቅ ልምድ። ጌታ የህጻን ጥምቀትን ኩነኔ ነው አለ (ሞሮኒ ፰፥፲–፳፩)። ልጆች የዋህ እና ኃጢያት የሌላቸው ናቸው። ተጠያቂ እስከሚሆኑ ድረስ ሰይጣን ልጆችን ለመፈተን ሀይል የለውም (ት. እና ቃ. ፳፱፥፵፮–፵፯) ስለዚህ ንስሀ መግባት ወይም መጠመቅ አያስፈልጋቸውም። ልጆች በስምንት አመት ላይ ይጠመቁ (ት. እና ቃ. ፷፰፥፳፭–፳፯)።