የሚስጥር ስብሰባ ደግሞም ቃየን; የጋድያንቶን ዘራፊዎች ተመልከቱ የቡድንን ክፉ አላማዎችን ለማከናወን በመሀላ አብረው የተሳሰሩ የሰዎች ድርጅት። የሀሰት አባት የሰው ልጆችን በግድያ የሚስጥር ሰብሰባ በጠበጠ, ፪ ኔፊ ፱፥፱. የጭለማ የሚስጥር ስራዎችን አጠፋ ዘንድ ያስፈልገኛል, ፪ ኔፊ ፲፥፲፭. የእግዚአብሔር ፍርድ በሚስጥራዊው ህብረት ላይ እንደዚህ መጣ, አልማ ፴፯፥፴. ጋድያንቶ የኔፊን ህዝብ መቡሉ ጥፋት ሊያመጣ ነበር, ሔለ. ፪፥፬–፲፫. ሰይጣን በህዝቡ ልብ ውስጥ የሚስጥር መሀላ እና ቃል ኪዳን እንዲሰሩ አደረጋቸው, ሔለ. ፮፥፳፩–፴፩. ጌታም በሚስጢራዊ ህብረት አይሰራም, ኤተር ፰፥፲፱. ሚስጢራዊ ህብረት የሚደግፍ ማንኛውም ሀገር ይጠፋል, ኤተር ፰፥፳፪–፳፫. እነርሱም በሚስጢራዊው ህብረት ምክንያት የነቢያቱን ቃላት በሙሉ አልተቀበሉም, ኤተር ፲፩፥፳፪. ከቃየን ቀናት ጀምሮ፣ ሚስጥር ህብረቶች ነበሩ, ሙሴ ፭፥፶፩.