ጄረም
በመፅሐፈ ሞርሞን ውስጥ፣ የኢኖስ ልጅ እና የሌሂ የልጅ ልጅ ልጅ። ከ፬፻፳–፫፻፷፩ ም.ዓ. ድረስ ለ፷ አመት የኔፋውያንን መዝገብ ጠበቀ (ኢኖስ ፩፥፳፭፤ ጄረም ፩፥፲፫)። በታሪካዊ መዝገቡ ላይ ብዙ ላለመጻፍ ውሳኔ ያደረገ ታማኝ ሰው ነበር (ጄረም ፩፥፪)።
መፅሐፈ ጄረም
በመፅሐፈ ሞርሞን ውስጥ በዚህ መፅሐፍ ውስጥ አስራ አምስት ቁጥሮች ብቻ ነው ያሉት። ጄረም ኔፋውያን በሙሴ ህግ ለመኖር እንደቀጠሉ እናም የክርስቶስ መምጣትን በጉጉት እንደሚጠብቁ መዘገበ። በእምነት ኃይለኛ ሰዎች በሆኑ ንጉሶች ይመሩም ነበር። ነቢያቸውን፣ ካህናታቸውን፣ እና መምሁራቸውን ሲያዳምጡ በለጸጉ።