ባል የሞተባት ደግሞም በጎ ድርገት ተመልከቱ ባሏ የሞተባት እና እንደገና ያላገባት ሴት። ያለ መጻተኛ ድሀ አደግም መበለትም መጥተው ይበላሉ, ዘዳግ. ፲፬፥፳፱. ደሀ መበለቲቱ ከጕድለትዋ የነበራትን ሁሉ ትዳርዋን ሁሉ ጣለች, ማር. ፲፪፥፵፩–፵፬. ወላጆች የሌላቸውን ልጆች ባልቴቶችንም በመከራቸው ጠይቅ, ያዕ. ፩፥፳፯. መበለቲቱንና ድሃ አደጉን በሚያስጨንቁ ላይ ጌታ ፈጣን ምስክር ይሆንባቸዋል, ፫ ኔፊ ፳፬፥፭ (ዘካ. ፯፥፲). ባል የሞተባቸው እና የሙት ልጆችም ይረዳሉ, ት. እና ቃ. ፹፫፥፮ (ት. እና ቃ. ፻፴፮፥፰).