ራዕይ
እግዚአብሔር በምድር ላይ ካሉት ልጆቹ ጋር የሚነጋገርበት። በመንፈስ ቅዱስ ሀይል በኩል የአንድ ድርጊት፣ ሰው፣ ወይም ነገር የሚታይ ራዕይ። ራዕይ በክርስቶስ ብርሀን ወይም በመንፈስ ቅዱስ በኩል በማነሳሳት፣ በራዕዮች፣ በህልሞች፣ ወይም በመላእክት በመጎብኘት ሊመጣ ይችላል። ራዕይ ታማኝን በሰለስቲያል መንግስት ወደ ዘለአለማዊ ደህናነት ለመምራት የሚችል መመሪያን ይሰጣል።
ጌታ ስራውን ለነቢያቱ ይገልጻል እናም ለነቢያቱ የተሰጡት ራዕዮች እውነት እንደሆኑም ለሚያምኑት ያረጋግጣል (ዓሞ. ፫፥፯)። በራዕይ በኩል፣ ጌታ ለሚፈልገው እና እምነት ላለው፣ ንስሀ ለገባው፣ እንዲሁም ለኢየሱስ ክርስቶስ ወንጌል ታዛዥ ለሆነው ለእያንዳንዱ ሰው መመሪያ ይሰጣል። ጆሴፍ ስሚዝ እንዳለው፣ “መንፈስ ቅዱስ ገላጭ ነው፣ ማንም ሰው ራዕይን ሳይቀበል መንፈስ ቅዱስን መቀበል አይችልም።”
በጌታ ቤተክርስቲያን ውስጥ፣ የቀዳሚ አመራር እና የአስራ ሁለቱ ሐዋሪያት ቡድን ለቤተክርስቲያኗ እና ለአለም ነቢያት፣ ባለራዕዮች፣ እና ገላጮች ናቸው። ጌታ ለቤተክርስቲያኗ ራዕይ ለመቀበል ስልጣን የሰጠው ለቤተክርስቲያኗ ፕሬዘደንት ብቻ ነው (ት. እና ቃ. ፳፰፥፪–፯)። እያንዳንዱ ሰው ለእራሱ ጥቅም ራዕይ ለመቀበል ይችላል።
ሕዝቅኤል ስለመጨረሻው ቀናት ያየው ራዕይ (ሕዝ. ፴፯–፴፱)፣ እስጢፋኖስ ኢየሱስን በእግዚአብሔር ቀኝ እጅ በኩል ቆሞ ያየው ራዕይ (የሐዋ. ፯፥፶፭–፶፮)፣ የመጨረሻው ቀናትን በሚመለከት ዮሐንስ ያየው ራዕይ (ራዕ. ፬–፳፩)፣ ሌሂ እና ኔፊ ስለህይወት ዛፍ ያዩት ራዕይ (፩ ኔፊ ፰፤ ፲–፲፬)፣ ዳግማዊ አልማ የጌታ መልአክን ያየበት ራዕይ (ሞዛያ ፳፯)፣ የያሬድ ወንድም የአለምን ኗሪዎችን ሁሉ ያየበት ራዕይ (ኤተር ፫፥፳፭)፣ የክብሮች ራዕይ (ት. እና ቃ. ፸፮) በከርትላንድ ቤተመቅደስ ውስጥ ጆሴፍ ስሚዝ እና ኦሊቨር ካውደሪ የተሰጣቸው ራዕይ (ት. እና ቃ. ፻፲)፣ ጆሴፍ ኤፍ ስሚዝ ስለሙታን ቤዣነት ያዩት ራዕይ (ት. እና ቃ. ፻፴፰)፣ ስለእግዚአብሔር እና ስለፍጥረቶቹ ለሙሴ የተሰጠ ራዕይ (ሙሴ ፩)፣ ስለእግዚአብሔር ሔሞክ ያየው ራዕይ (ሙሴ ፮–፯)፣ እና የጆሴፍ ስሚዝ የመጀመሪያ ራዕይ (ጆ.ስ.—ታ. ፩)።