ወሊድ መቆጣጠሪያ ደግሞም ቤተሰብ; ጋብቻ፣ መጋባት ተመልከቱ ፅንስን በመቆጣጠር ወይም በመከላከል ለተጋቡት የሚወለዱትን ልጆች ቁጥር መቆጣጠር። ብዙ፥ ተባዙ፥ ምድርንም ሙሉአት, ዘፍጥ. ፩፥፳፰ (ሙሴ ፪፥፳፰). ልጆች የእግዚአብሔር ቅርስ ናቸው, መዝ. ፻፳፯፥፫–፭. የሌሒ ቤተሰብ ለጌታ ዘር ያሳድጉ, ፩ ኔፊ ፯፥፩. ጋብቻ ለሰው በእግዚአብሔር የተመደበ ነው, ት. እና ቃ. ፵፱፥፲፭–፲፯. ከፍ ከፍ ያሉት ሙሉነትን እና የዘር ቀጣይነትን ለዘለአለም ይቀበላሉ, ት. እና ቃ. ፻፴፪፥፲፱፣ ፷፫.