ሄሮድስ
በኢየሱስ ክርስቶስ ዘመን አካባቢ በይሁዳ ውስጥ መሪዎች የነበሩ ቤተሰቦች። በብዙዎቹ የአዲስ ኪዳን ድርጊቶች እነርሱ አስፈላጊ ሰዎች ነበሩ። ቤተሰቡ የተጀመረው ስለአዳኝ መወለድ በፈራው (ማቴ. ፪፥፫) እና በቤተልሔም ህጻናት እንዲገደሉ ትእዛዝ በሰጠው በታላቁ ሄሮድስ ነበር። ወንድ ልጅቹም አርስጣባሉ፣ ሄሮድስ ፊልጶስ (ማቴ. ፲፬፥፫፤ ማር. ፮፥፲፯)፤ የአራተኛው ክፍል ገዥ ሄሮድስ አንቲጳስ (ማቴ. ፲፬፥፩፤ ሉቃ. ፱፥፯፤ ደግሞም ንጉስ ሄሮድስ ተብሎ የሚታወቀው፣ ማር. ፮፥፲፬)፤ አርኪልዎስ (ማቴ. ፪፥፳፪)፤ እና ፊልጶስ፣ የአራተኛው ክፍል ገዥ (ሉቃ. ፫፥፩) ነበሩ። ሄሮድስ አግሪጳ ቀዳማዊ (የሐዋ. ፲፪፥፩–፳፫) እና እህቱ ሄሮድያዳ (ማቴ. ፲፬፥፫፤ ማር. ፮፥፲፯) የአርስጣባሉ ልጆች ነበሩ። ሄሮድስ አግሪጳ ቀዳማዊም በአዲስ ኪዳን ውስጥ የተጠቀሱ ብዙ ልጆች ነበሩት፣ እነርሱም ሄሮድስ አግሪጳ ካልዕ (የሐዋ. ፳፭፥፲፫)፣ በርኒቄ (የሐዋ. ፳፭፥፲፫)፣ እና ድሩሲላ፣ የፊልክስ ባለቤት (የሐዋ. ፳፬፥፳፬) ነበሩ።