አሞን፣ የሞዛያ ወንድ ልጅ ደግሞም ሞዛያ፣ የቢንያም ልጅ; አንቲ-ኔፊ-ሌሂ; የሞዛያ ልጆች ተመልክቱ በመፅሐፈ ሞርሞን ውስጥ፣ የንጉስ ሞዛያ ወንድ ልጅ። አሞን ትጋታዊ ጥረቱ ብዙ መንፈሶችን ወደ ክርስቶስ ለመቀየር እንደረዳ ሚስዮን አገለገለ። ቤተክርስትያኗን ለማጥፋት የፈለገ አረመኔ ነበር, ሞዛያ ፳፯፥፰–፲፣ ፴፬. ለእርሱ እና ለጓደኞቹ መላእክት ተገለጠላቸው, ሞዛያ ፳፯፥፲፩. ንስሀ ገባ እና የእግዚአብሔርን ቃል መስበክ ጀመረ, ሞዛያ ፳፯፥፴፪–፳፰፥፰. በንጉስነት ለመመደብ እንቢ አለ እና በምትኩ የእግዚአብሔርን ቃል ለመስበክ ወደ ላማናውያን ምድር ሄደ, አልማ ፲፯፥፮–፱. ለመመሪያ ጾመ እና ጸለየ, አልማ ፲፯፥፰–፲፩. ታስሮ ወደ ንጉስ ላሞኒህ ተወስዶ ነበር, አልማ ፲፯፥፳–፳፩. የላሞኒህን መንጋዎች አዳነ, አልማ ፲፯፥፳፮–፴፱. ለላሞኒህ ሰበከ, አልማ ፲፰፥፩–፲፱፥፲፫. እግዚአብሔርን አመሰገነ እና በደስታ ተሸነፈ, አልማ ፲፱፥፲፬. በእርሱ የተቀየሩት በምንም አልከዱም, አልማ ፳፫፥፮. ሺዎችን ወደ እውነት ለማምጣት በእግዚአብሔር እጆች መሳሪያ ስለሆነ ተደሰተ, አልማ ፳፮፥፩–፰ (አልማ ፳፮). የአንቲ-ኔፊ-ሌሂ ህዝቦችን መራ, አልማ ፳፯. ከአልማ ጋር በመገናኘቱ ታላቅ ደስታ ተሰማው, አልማ ፳፯፥፲፮–፲፰.