የተሰበረ ልብ ደግሞም ልብ; መስዋዕት; መጸጸት፣ ንስሀ መግባት; ትሁት፣ ትሕትና; ገር፣ ገርነት ተመልከቱ የተሰበረ ልብ መኖር ትሁት፣ የተጸጸተ፣ ንስሀ የገባ፣ እና የዋህ መሆን ማለት ነው—ያም ለእግዚአብሔር ፈቃድ ተቀባይ መሆን ነው። የተቀጠቀጠና የተዋረደ መንፈስ ካለው ጋር እኖራለሁ, ኢሳ. ፶፯፥፲፭. ክርስቶስ የተሰበረ ልብና የተዋረደ መንፈስ ላላቸው እራሱን አቀረበ, ፪ ኔፊ ፪፥፯. ለጌታ እንደ መስዋዕት የተሰበረ ልብ እና የተዋረደ መንፈስ አቅርቡ, ፫ ኔፊ ፱፥፳ (ት. እና ቃ. ፶፱፥፰). ልባቸው የተሰበረና መንፈሳቸው የተዋረደ ብቻ ናቸው ወደ ጥምቀት የተቀበሉት, ሞሮኒ ፮፥፪. ኢየሱስ የተሰቀለው ልባቸው ለተዋረደው ኃጢያት ስርየት ነው, ት. እና ቃ. ፳፩፥፱. መንፈሱ የተዋረደው ተቀባይ ነው, ት. እና ቃ. ፶፪፥፲፭. ለተዋረዱት መንፈስ ቅዱስ ቃል ተገብቷል, ት. እና ቃ. ፶፭፥፫. መንፈሴ ትሁቱን እና የተዋረደውን ለማብራራት ተልኳል, ት. እና ቃ. ፻፴፮፥፴፫.