ሀላፊነት፣ ሀላፊ ደግሞም መሾም፣ ሹመት; ክህነት ተመልከቱ በድርጅት ውስጥ ያለ ስልጣን፣ ብዙ ጊዜ በቅዱሣት መጻህፍት ውስጥ የክህነት ሀላፊነትን ለመጠቆም የሚጠቀሙበት ነው፤ ይህም ለስራ ደረጃው የተመደበ ሀላፊነትን ወይም የስራ ደረጃን የሚይዘውን ሰው የሚጠቁም ሊሆንም ይችላል። የአባላት ሁሉ ሥራ አንድ እንዳይደለ, ሮሜ ፲፪፥፬. ኃላፊነታችንን ለጌታ አጎላን, ያዕቆ. ፩፥፲፱. መልከ ፄዴቅ የሊቀ ካህንነት ሀላፊነትን ተቀበለ, አልማ ፲፫፥፲፰. የመላእክት አገልግሎት ኃላፊነታቸው ሰዎችን ወደ ንሰሃ መጥራት ነው, ሞሮኒ ፯፥፴፩. ካለቤተክርስቲያኗ ምርጫ ማንም ሰው በቤተክርስቲያን ሀላፊነት አይሾምም, ት. እና ቃ. ፳፥፷፭. እያንዳንዱ ሰው በተሾመበት ይቁም, ት. እና ቃ. ፹፬፥፻፱. ፕሬዘደንቶች፣ ወይም ከተለያዩ ከእነዚህ የክህነት ስልጣኖች ውስጥ በተላያዩ ሀላፊነቶች ከተሾሙት መካከል የሚመጡ ወይም የሚሾሙ መሪዎች አሉ, ት. እና ቃ. ፻፯፥፳፩. የክህነት ቡድኖችን የሚመሩት ሀላፊነቶች ተገልጸዋል, ት. እና ቃ. ፻፯፥፹፭–፺፰. እያንዳንዱም ወንድ ሰው ሀላፊነቱን እና በተመደበበት ሀላፊነት በቅንነት መስራትን ይማር, ት. እና ቃ. ፻፯፥፺፱–፻. ለእናንተ ለክህነት ስልጣኔ አባል የሆኑትን ባለስልጣኖች እሰጣችኋለሁ, ት. እና ቃ. ፻፳፬፥፻፳፫.