የጥናት እርዳታዎች
ስሚዝ፣ ጆሴፍ ዳግማዊ


ስሚዝ፣ ጆሴፍ ዳግማዊ

የኢየሱስ ክርስቶስ እውነተኛ ቤተክርስቲያንን በምድር ላይ በዳግም ለመመለስ የተመረጠ ነቢይ። ጆሴፍ ስሚዝ በዩናይትድ ስቴትስ ኦፍ አሜሪካ በቨርሞንት ስቴት ውስጥ ተወለደ እናም ከ፲፰፻፭ እስከ ፲፰፻፵፬ (እ.አ.አ.) ድረስ በህይወት ኖረ።

በ፲፰፻፳ (እ.አ.አ.)፣ እግዚአብሔር አብ እና ኢየሱስ ክርስቶስ በጆሴፍ ታዩ፣ እናም በምድር ካሉት ቤተክርስቲያኖች መካከል ማንኛቸውም እውነተኛ እንዳልሆኑ ተማረ (ጆ.ስ.—ታ. ፩፥፩–፳)። በኋላም በአሜሪካ ክፍለ አህጉር ላይ ይኖሩ የነበሩ የጥንት ህዝቦችን መዝገብ የያዘውን የወርቅ ሰሌዳ የተደበቀበትን ቦታ በገለጸለት በመልአክ ሞሮኒ ተጎበኘ (ጆ.ስ.—ታ. ፩፥፳፱–፶፬)።

ጆሴፍ የወርቅ ሰሌዳዎችን ተረጎመ እናም በ፲፰፻፴ (እ.አ.አ.) እንደ መፅሐፈ ሞርሞን አተማቸው (ጆ.ስ.—ታ. ፩፥፷፮–፷፯፣ ፸፭)። በ፲፰፻፳፱ (እ.አ.አ.)፣ ክህነትን ከመጥምቁ ዮሐንስ፣ እናም ከጴጥሮስ፣ ከያዕቆብ፣ እና ከዮሐንስ ተቀበሉ። (ት. እና ቃ. ፲፫፳፯፥፲፪፻፳፰፥፳ጆ.ስ.—ታ. ፩፥፷፰–፸)።

በእግዚአብሔር እንደተመራም፣ በሚያዝያ ፮፣ ፲፰፻፴ (እ.አ.አ.) ጆሴፍ እና ብዙ ሌሎች ዳግም የተመለሰችውን የኢየሱስ ክርቶስ ቤተክርስቲያን አደራጁ። (ት. እና ቃ. ፳፥፩–፬)። በጆሴፍ አመራር፣ በካናዳ፣ በእንግሊዝ፣ እና በዮናይትር ስቴትስ በምስራቅ ክፍሎች፣ በልዩም በኦሀዮ፣ በምዙሪ፣ እናም በኢለኖይ ውስጥ፣ ቤተክርስቲያኗ አደገች። ጠንካራ መሳደድ ጆሴፍን እና ቅዱሳንን የትም በሚሰፍሩበት ቦታዎች ሁሉ ተከተሏቸው። በሰኔ ፳፯፣ ፲፰፻፵፬ (እ.አ.አ.)፣ ጆሴፍ እና ወንድሙ ሀይረም በካርቴጅ ኢለኖይ፣ በዩናይትድ ስቴትስ ኦፍ አሜሪካ ውስጥ ሰማዕት ሆኑ።

በነቢዩ ጆሴፍ ስሚዝ የመጡ ቅዱሣት መጻህፍት

ጆሴፍ በመልአክ ሞሮኒ የተሰጡትን የወርቅ ሰሌዳዎችን ክፍል ተረጎመ፣ ይህም ትርጉም በ፲፰፻፴ (እ.አ.አ.) እንደ መፅሐፈ ሞርሞን ታተመ። መሰረታዊ ትምህርቶችን እና የቤተክርስቲያኗን ድርጅቶች ዋና ሀሳቦችን የሚሰጡ ብዙ ራዕዮችንም ከጌታ ተቀበለ። ከእነዚህ ራዕዮች ብዙዎቹ አሁን ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች ተብለው በሚታወቁት ውስጥ ተካለሱ። የሙሴ፣ የአብርሐም፣ እና የማቴዎች የተነሳሱ ትርጉሞችን፣ ከእራሱ ታሪክና ምስክሮች ክፍሎችን፣ እና የቤተክርስቲያኗን ትምህርት እና እምነት የያዙ አስራ ሶስት መረጃዎችን የያዘውን የታላቅ ዋጋ ዕንቁንም የማምጣት ሀላፊ የሆነ ነበር።