አዲስ ኪዳን
ስለኢየሱስ ክርስቶስ፣ ስለሐዋሪያት፣ እና ስለኢየሱስ ክርስቶስ ተከታዮች ህይወት እና አገልግሎት የሚገልጹ (በግሪክ ቋንቋ በመጀመሪያ የተጻፉ) የተነሳሱ ጽሁፎች። አዲስ ኪዳን በወንጌሎች፣ በሐዋርያት ስራ፣ በጳውሎስ መልእክቶች፣ አጠቃላይ መልእክቶች፣ እና በራዕይ መፅሐፍ የተከፋፈሉ ናቸው።
አራቱ ወንጌሎች፣ የማቴዎስ፣ የማርቆስ፣ የሉቃስ፣ እና የዮሐንስ መፅሐፎች የክርስቶስ ህይወት ታሪኮች ናቸው። የሐዋርያት ስራ የቤተክርስቲያኗን እና የሐዋሪያትን፣ በልዩም ከክርስቶስ ሞት በኋላ የጳውሎስን የሚስዮን ጉዞ ታሪክ ይመዘግባል። የጳውሎስ ደብዳቤዎች የቤተክርስቲያኗን መሪዎችና አባላት ያስተምራል። ሌሎቹ ደብዳቤዎች የተጻፉት በሌሎች ሐዋሪያት ነበር እናም የመጀመሪያ ቅዱሳንን ተጨማሪ ምክር የሚሰጥ ነበር። በሐዋሪያው ዮሐንስ የተጻፈው የዮሐንስ ራዕይ ስለመጨረሻ ቀናት ትንቢቶችን የያዘ ነው።