ኢሳይያስ
ከ፯፻፵–፯፻፩ ም.ዓ. ድረስ የተነበየ የብሉይ ኪዳን ነቢይ። እንደ ንጉስ ሕዝቅያስ ዋና አማካሪ፣ ኢሳይያስ ታላቅ የሀይማኖትና የፖለቲካ ተፅዕኖ ነበረው። ኢሳይያስ በአብርሐም ቀናት ይኖር የነበረ ነቢይ ነበር (ት. እና ቃ. ፸፮፥፻፤ ፹፬፥፲፫)።
ኢየሱስ ኢሳይያስን ከሌሎች ነቢያት በላይ ጠቅሶ ነበር። ደግሞም ኢሳይያስ በአዲስ ኪዳን ውስጥ በጴጥሮስ፣ ዮሐንስ፣ እና ጳውሎስ ተጠቅሷል። መፅሐፈ ሞርሞንና ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች ተጨማሪ ጠቅሶች ከሌሎች ነቢያት በላይ ከኢሳይያስ አሏቸው እናም ኢሳይያስን ለመረዳት ብዙ እርዳታዎችን ያቀርባሉ። ኔፊ ከኢሳይያስ ጽሁፎች ህዝቡን አስተማረ (፪ ኔፊ ፲፪–፳፬፤ ኢሳ. ፪–፲፬)። ጌታ ለኔፋውያን “የኢሳይያስ ቃላት ታላቅ ናቸው” እናም ኢሳይያስ የተነበያቸው ሁሉም ነገሮች እንደሚሟሉ ነገራቸው (፫ ኔፊ ፳፫፥፩–፫)።
መፅሐፈ ኢሳይያስ
የብሉይ ኪዳን መፅሀፍ። ብዙዎቹ የኢሳይያስ ትንቢቶች ስለአዳኝ መምጣት፣ ስለምድራዊ አገልግሎቱና (ኢሳ. ፱፥፮) በመጨረሻ ቀን እንደ ታላቅ ንጉስ መምጣቱ (ኢሳ. ፷፫) የሚናገሩ ነበሩ። ደግሞም ስለእስራኤል ወደፊት ሁኔታም ብዙ ተነበየ።
ምዕራፍ ፩ መፅሐፉን በሙሉ ማስተዋወቂያ ነው። ኢሳይያስ ፯፥፲፬፤ ፱፥፮–፯፤ ፲፩፥፩–፭፤ ፶፫፤ እና ፷፩፥፩–፫ የአዳኝ ተልዕኮን አስቀድመው ይናገራሉ። ምዕራፍ ፪፣ ፲፩፣ ፲፪፣ እና ፴፭ ወንጌሉ ዳግም በሚመለስበት፣ እስራኤል በምትሰበሰብበት፣ እና የጠማው ምድር እንደ ጽጌ ረዳም በሚያብብበት በኋለኛው ቀናት ስለሚሆኑ ጉዳዮች ይናገራሉ። ምዕራፍ ፳፱ ስለመፅሐፈ ሞርሞን መምጣት ትንቢት የያዘ ነው (፪ ኔፊ ፳፯) ምዕራፍ ፵–፵፮ ስለያህዌህ እንደ እውነተኛ አምላክ የጣዖት አምላኪዎች አምልክት በላይ ታላቅነት የሚያውጁ ነበሩ። የሚቀሩት ምዕራፍ፣ ፵፯–፷፮፣ ስለእስራኤል የመጨረሻ ዳግም መመለስ እና ጌታ በህዝቡ መካከል በመኖር ስለፅዮን መመስረት ይናገራሉ።