ቅዱሳት መጻህፍት
፪ ኔፊ ፲፪


ምዕራፍ ፲፪

ኢሳይያስ የኋለኛውን ቀን ቤተመቅደስ፤ የእስራኤልን መሰብሰብና የአንድ ሺህ ዘመን ፍርድን እና ሰላምን ተመለከተ—በዳግም ምፅአቱ ኩራተኞችና ኃጢአተኞች ትሁት ይሆናሉ—ኢሳይያስ ፪ አነጻፅሩ። ከ፭፻፶፱–፭፻፵፭ ም.ዓ. ገደማ።

የአሞጽ ልጅ ኢሳይያስ ስለ ይሁዳና ስለ ኢየሩሳሌም ያየው ቃል—

እናም በኋለኛው ቀናት እንዲህ ይሆናል፣ የጌታ ቤት ተራራ በተራሮች ጫፍ ላይ ሲመሰረት፣ እናም ከኮረብቶችም በላይ ከፍ ሲል፣ ህዝቦችም ሁሉ ወደ እርሱ ይሰበሰባሉ።

ከእዚያም ብዙ ህዝብ ሄደው እንዲህ ይላል፣ ኑና ወደ ጌታ ተራራ ወደ ያዕቆብ አምላክ ቤት እንውጣ፤ እናም እርሱ መንገዱን ያስተምረናልና፣ በጎዳናው እንራመዳለንህግ ከፅዮን፣ የጌታም ቃል ከኢየሩሳሌም ይወጣልና።

እናም እርሱ በሃገሮች መካከል ይፈርዳል፣ ብዙ ህዝቦችንም ይገስፃል፣ እናም ሰይፋቸውን ማረሻ፣ ጦራቸውንም ማጭድ ለማድረግ ይቀጠቅጣሉ—ሀገርም በሃገር ላይ ሰይፍ አያነሳም፣ ጦርነትም ከእንግዲህ ወዲህ አይማሩም።

የያዕቆብ ቤት ሆይ፣ ኑ በጌታ ብርሃን እንራመድ፤ አዎን፣ ኑ ሁላችሁም ተቅበዝብዛችኋልና፣ እያንዳንዱም በኃጢያት ወደገዛ መንገዱ አዘነበለ።

ስለዚህ፣ አቤቱ ጌታ፣ ሕዝብህን የያዕቆብን ቤት ትተሃል፣ ምክንያቱም እነርሱ የምስራቅን ሰዎች ልምድ ስለተሞሉና፣ እንደ ፍልስጤማውያን ምዋርተኞችን ስለሚያዳምጡ፣ እና በባዕድ ልጆች እራሳቸውን ስላስደሰቱ ነው።

ምድራቸውም ደግሞ በብርና በወርቅ ተሞልታለች፣ ለመዛግብቶቻቸውም ፍጻሜ የለውም፤ ምድራቸውም ደግሞ በፈረሶች ተሞልታለች፣ ሰረገሎቻቸውም ፍፃሜ የላቸውም።

ምድራቸውም ደግሞ በጣዖት ተሞልታለች፤ በጣቶቻቸውም ለሰሩት ለእጃቸው ስራ ይሰግዳሉ።

እናም ተራው ሰው አልሰገደም፣ እናም ታላቁም ሰው እራሱን ትሁት አላደረገም፣ ስለዚህ፣ ይቅር አትበለው።

እናንተ ክፉዎች ሆይ ወደ ድንጋዩ ዋሻ ግቡ፣ እናም በመሬት ውስጥም ተሸሸጉ፣ ምክንያቱም የጌታ ፍርሃትና የክብሩ ሞገስ ክብሩ ይመታችኋል።

፲፩ እናም እንዲህ ሆነ ኩራት የሆነው የሰው አመለካከት አልባሌ ይሆናል፣ የሰዎችም ትዕቢት ዝቅ ትላለች፣ እናም ጌታ ብቻውን በዚያ ቀን ከፍ ከፍ ይላል።

፲፪ የሰራዊት ጌታ ቀን በሁሉም ሀገር ላይ፣ አዎን፣ በማንኛውም ላይ፣ አዎን፣ በትዕቢተኛውና በኩራተኛው ላይና፣ ከፍ ባለውም ላይ ሁሉ በቅርቡ ይመጣልና፣ እናም እርሱም ይዋረዳል።

፲፫ አዎን፣ እናም የጌታ ቀን በሊባኖስ ዝግባዎች ላይ ሁሉ ይመጣል፣ ምክንያቱም እነርሱ ከፍና ኮራ ብለዋልና፤ እናም በበሳንም ዛፍ ሁሉ ላይ፤

፲፬ እናም ከፍ ባሉት ተራሮች ላይ ሁሉ፣ እናም በኮረብታዎች ላይ ሁሉ፣ እና በኮሩት ሀገሮች ሁሉ ላይ፣ እናም በማንኛውም ሀገር ላይ፤

፲፭ እናም በማንኛውም ረጅም ግንብና፣ በተመሸገውም ቅጥር ላይ ይመጣል፤

፲፮ እናም በባህሩ መርከቦች ላይ ሁሉና፣ በተርሴስ መርከብ ላይ ሁሉ፣ እናም አስደሳች ምስሎች ላይ ሁሉ።

፲፯ እናም የሰው የኩራት አመለካከት ይወድቃልና፣ የሰዎች ዕብሪትም ይዋረዳል፤ እናም በዚያም ቀን ጌታ ብቻውን ከፍ ከፍ ይላል።

፲፰ እናም ጣዖቶችን ፈፅሞ ያጠፋል።

፲፱ እናም እነርሱ ጌታ ምድርን በከፍተኛ ሁኔታ ያናውጥ ዘንድ በተነሣ ጊዜ ወደ ድንጋይ ጉድጓዶችና፣ ወደ ምድር ዋሻዎች ይገባሉ፣ የጌታ ፍርሃት ይመጣባቸዋልና፣ እናም የእርሱ ግርማ ሞገሱ ክብር ይመታቸዋልና።

በዚያም ቀን ሰው ይሰግድላቸው ዘንድ ያበጃቸውን የብር ጣዖቶቹን፣ እና የወርቁን ጣዖቶቹን ለፍልፈልና ለሌሊት ወፍ ይጥላል

፳፩ ጌታ ምድርን በከፍተኛ ሁኔታ ያናውጥ ዘንድ በተነሳ ጊዜ፣ የጌታ ፍርሃት ስለሚመጣባቸው፣ እናም የእርሱ ግርማ ሞገሱ ክብር ስለሚመታቸው ወደ ተሰነጣጠቁ የድንጋይ ዋሻና ወደ ፍርስራሽ ዓለቶች ጫፍ ይገባሉ።

፳፪ እስትንፋሱ በአፍንጫው ያለበትን ሰው ተዉት፣ እርሱ ስለ ምን ይቈጠራል?