ቅዱሳት መጻህፍት
፪ ኔፊ ፲፮


ምዕራፍ ፲፮

ኢሳይያስ ጌታን አየ—የኢሳይያስ ኃጢአቶች ይቅር ተብለዋል—እንዲተነብይ ተጠርቷል—አይሁዶች የኢየሱስን ትምህርት እንደሚያስወግዱ ተንብዮአል—ቅሪቶች ይመለሳሉ—ኢሳይያስ ፮ን አነጻፅሩ። ፭፻፶፱–፭፻፵፭ ም.ዓ. ገደማ።

ንጉስ ኡዝያን በሞተበት ዓመት፣ ጌታ ደግሞ በረጅምና ከፍ ባለ ዙፋን ላይ ተቀምጦ አየሁት፣ የልብሱም ዘርፍ መቅደሱን ሞልቶት ነበር።

ሱራፌልም ከእርሱ በላይ ቆመው ነበር፤ እያንዳንዱ ስድስት ክንፍ ነበረው፤ በሁለቱ ክንፍ ፊቱን ሸፈነ፣ እናም በሁለቱ ክንፍ እግሮቹን ሸፈነ፣ እናም በሁለቱ ክንፍ ይበር ነበር።

እናም አንዱ ለሌላኛው፥ ቅዱስ፣ ቅዱስ፣ ቅዱስ ነው የሰራዊት ጌታ፤ ምድር ሁሉ በክብሩ ተሞልታለች፤ እያለ ይጮህ ነበር።

እናም የመዝጊያው ምሶሶ በጮኸው ድምፅ ተናወጠ፣ እናም ቤቱ ጭስ ሞላበት።

ከዚያም እኔ አልኩ፥ ወየው ለእኔ! የተበላሸሁ ነኝና፤ ምክንያቱም እኔ ከንፈረ-እርኩስ ነኝ፤ እናም ከንፈሮቻቸው በረከሰ ሕዝቦች መካከል እኖራለሁ፤ ዐይኖቼም ንጉሱን፣ የሰራዊት ጌታን አይተዋልና።

ከሱራፌልም አንዱ ወደ እኔ እየበረረ መጣ፣ በእጁም ከመሰዊያው በጉጠት የወሰደው ፍም ነበር፤

እናም በአፌ ላይ አደረገው፣ እናም አለ፥ እነሆ፣ ይህ ከንፈሮችህን ነክቷል፣ በደልህም ከአንተ ተወስዶአል፣ ኃጢያትህም ተሰርዮልሀል።

ደግሞም የጌታን ድምፅ እንዲህ ሲል ሰማሁት፥ ማንን እልካለሁ፣ እናም ለእኛስ ማን ይሂድልን? እናም እኔ እንዲህ አልኩ፥ እነሆኝ፤ እኔን ላከኝ።

እናም እርሱ አለኝ፥ ሂድና ይህንን ህዝብ ተናገራቸው—በእርግጥ ስሙ፣ ነገር ግን አይገባቸውም፤ እንዲሁም በእርግጥ እዩ፣ ነገር ግን አይገነዘቡም።

የህዝቡን ልብ አደንድን፣ እናም ጆሮአቸውንም እንዳይሰማ፣ ዐይናቸውንም እንዳያዩ አድርግ—በዐይኖቻቸው እንዳያዩና በጆሮአቸውም እንዳይሰሙ፣ እናም በልባቸው እንዳያስተውሉና፣ ተመልሰውም እንዳይፈወሱ አድርግ።

፲፩ ከዚያም እኔ ጌታን እስከመቼ ድረስ ነው አልሁ? እናም እርሱ ከተሞች የሚኖሩባቸውን አጥተው እስኪፈርሱ፣ እና ቤቶችም ያለሰውና፣ ምድርም ፈፅሞ ባልጩት እስክትሆን ድረስ ነው አለኝ፤

፲፪ እግዚአብሔርም ሰዎችን እስኪያርቅ፥ በምድርም መካከል ውድማው መሬት ይበዛልና።

፲፫ ነገር ግን አንድ አስረኛው ይቀራል፣ እናም እነርሱ ይመለሳሉ፣ ቅጠሎቻቸውን ሲጥሉም ጉቶዎቻቸው በውስጣቸው እንደነበሩት ግራር እና እንደኮምበል ዛፍ ይበላሉም፣ ስለዚህ የተቀደሰው ዘር በዚያው ጉቶው ይሆናል።

      • ይህም በ፯፻፶ ም.ዓ. አካባቢ ማለት ነው።

      • ይህም የልብሱ ጠርዝ ቅምቅማት፣ ወይም የዚህ ጫፍ ማለት ነው።

      • ዕብ. የመግቢያ በር መሰረት ተንቀጠቀጠ።

      • ዕብ. መቆረጥ፣ ይህም በእራሱ እና በህዝቡ ኃጢያት ህሊናው ተሸንፎ ነበር ማለት ነው።

      • ይህም የማፅዳት ምሳሌ ማለት ነው።

      • ይህም እንደ ዛፍ፣ ምንም እንኳን ቅጠሎቹ የተበተኑ ቢሆኑም፣ ህይወቱና ፍሬ የማፍራት ችሎታ በውስጥ አለው ማለት ነው።