የኢየሱስ ክርስቶስ ዳግም ምፅዓት ደግሞም ማጎግ; አርማጌዶን; ኢየሱስ ክርስቶስ; የጊዜዎች ምልክቶች; ጎግ ተመልከቱ በአንድ ዚህ አመት ዘመን መጀምሪያ ላይ፣ ክርስቶስ ወደ ምድር ይመለሳል። ይህም ድርጊት የምድርን ስጋዊ የሙከራ ጊዜ መጨረሻን ይጠቁማል። ኃጢያተኞች ከምድር ይወጣሉ እናም ምድር በምትጸዳበት ጊዜ ጻድቃን በዳመና ይነጠቃሉ። ክርስቶስ መቼ ለሁለተኛ ጊዜ እንደሚመጣ ማንም ሰው ባያውቅም፣ ጊዜው እየቀረበ እንደሆነ የምንመለከታቸው ምልክቶች ሰጥቶናል፣ (ማቴ. ፳፬፤ ጆ.ስ.—ማቴ. ፩)። እኔን ግን የሚቤዠኝ ሕያው እንደ ሆነ፥ በመጨረሻም ዘመን በምድር ላይ እንዲቆም አውቃለሁ, ኢዮብ ፲፱፥፳፭. ጕልበት ሁሉ ለእኔ ይንበረከካል፥ ምላስም ሁሉ በእኔ ይምላል, ኢሳ. ፵፭፥፳፫ (ት. እና ቃ. ፹፰፥፻፬). የሰው ልጅ ከሰማይ ደመናት ጋር መጣ, ዳን. ፯፥፲፫ (ማቴ. ፳፮፥፷፬; ሉቃ. ፳፩፥፳፭–፳፰). ወደ እርሱም ወደ ወጉት ይመለከታሉ, ዘካ. ፲፪፥፲. ሰውም። ይህ በእጅህ መካከል ያለ ቍስል ምንድር ነው? ይለዋል, ዘካ. ፲፫፥፮ (ት. እና ቃ. ፵፭፥፶፩). እርሱ እንደ አንጥረኛ እሳትና ነውና የሚመጣበትን ቀን መታገሥ የሚችል ማን ነው, ሚል. ፫፥፪ (፫ ኔፊ ፳፬፥፪; ት. እና ቃ. ፻፳፰፥፳፬). የሰው ልጅ በአባቱ ክብር ይመጣል, ማቴ. ፲፮፥፳፯ (ማቴ. ፳፭፥፴፩). ስለዚያች ቀንና ስለዚያች ሰዓት ግን ከአባት ብቻ በቀር የሚያውቅ የለም, ማቴ. ፳፬፥፴፮ (ት. እና ቃ. ፵፱፥፯; ጆ.ስ.—ማቴ. ፩፥፴፰–፵፰). ይህ ኢየሱስ ወደ ሰማይ ሲሄድ እንዳያችሁት፥ እንዲሁ ይመጣል, የሐዋ. ፩፥፲፩. ጌታ ራሱ ከሰማይ ይወርዳልና, ፩ ተሰ. ፬፥፲፮. የጌታው ቀን ግን እንደ ሌባ ሆኖ ይመጣል, ፪ ጴጥ. ፫፥፲. ጌታ ከብዙ ሺህ ቅዱሳኑ ጋር ይመጣል, ይሁዳ ፩፥፲፬. ከደመና ጋር ይመጣል፤ ዓይንም ሁሉ ያዩታል, ራዕ. ፩፥፯. ኢየሱስ አመምን ለመፍረድ ይቆማል, ፫ ኔፊ ፳፯፥፲፬–፲፰. ተዘጋጁ ተዘጋጁ፤ ጌታ ተቃርቧልና, ት. እና ቃ. ፩፥፲፪. ራሴን ከሰማይ በኃይል እገልጣለሁ፣ በምድር ላይ ለአንድ ሺ አመታት እኖራለሁ, ት. እና ቃ. ፳፱፥፱–፲፪. ድምጻችሁን ከፍ አድርጉ እናም ንስሀ መግባትን ጩሁ፣ የጌታን መንገድ ለዳግም ምፅዓቱ አዘጋጁ, ት. እና ቃ. ፴፬፥፭–፲፪. እኔ ኢየሱስ ክርስቶስ ነኝ፤ እናም በድንገትም ወደ ቤተመቅደሴ እመጣለሁ, ት. እና ቃ. ፴፮፥፰ (ት. እና ቃ. ፻፴፫፥፪). የምታዩኝ ቀን በቶሎም ይምጣል፣ እናም እኔም እንደሆንኩ ታውቃላችሁ, ት. እና ቃ. ፴፰፥፰. እኔን የሚፈራም ስለጌታ መምጫ ታላቅ ቀን፣ እንዲሁም የሰው ልጅ መምጫ ምልክቶችን፣ ይጠብቃል, ት. እና ቃ. ፵፭፥፴፱. የጌታ ፊትም ይገለጻል, ት. እና ቃ. ፹፰፥፺፭. ታላቁና የሚያስፈራው የጌታ ቀን ቅርብ ነው, ት. እና ቃ. ፻፲፥፲፮. አዳኝ በሚመጣበት ጊዜ እርሱ እንዳለ እናየዋለን, ት. እና ቃ. ፻፴፥፩. አዳኝ፣ በህዝቦቹ መካከል ይቆማል፣ እና በሁሉም ስጋዎች መካከል ይነግሳል, ት. እና ቃ. ፻፴፫፥፳፭. ከእግዚአብሔር ከሰማይ ውስጥ የወረደው፣ ልብሱም የቀላ ከባሶራ የሚመጣ ማን ነው, ት. እና ቃ. ፻፴፫፥፵፮ (ኢሳ. ፷፫፥፩).