ዚኖስ ስለክርስቶስ ተልዕኮ የተነበየ በብሉይ ኪዳን ዘመን በመፅሐፈ ሞርሞን ውስጥ ብቻ የተጠቀሰ የእስራኤል ነቢይ። ስለክርስቶስ መቀበር እና ስለሶስት ቀን ጭለማ ተነበየ, ፩ ኔፊ ፲፱፥፲፣ ፲፪. ስለእስራኤል መሰብሰብ ተነበየ, ፩ ኔፊ ፲፱፥፲፮. ያዕቆብ ከዚኖስ ስለለማው እና ስለዱር የወይራ ዛፍ ታሪክ ጠቀሰ, ያዕቆ. ፭. ያዕቆብ የዚኖስን ምሳሌ አብራራ, ያዕቆ. ፮፥፩–፲. ጸሎትን እና አምልኮን በሚመለከት አስተማረ, አልማ ፴፫፥፫–፲፩. ቤዛነት የሚመጣው በወልድ በኩል እንደሆነ አስተማረ, አልማ ፴፬፥፯. ለደፋር ምስክሩ ተገደለ, ሔለ. ፰፥፲፱. ስለላማናውያን ዳግም መመለስ ተመለሰ, ሔለ. ፲፭፥፲፩. በክርስቶስ ሞት ስለሚመጣው ጥፋት መሰከረ, ፫ ኔፊ ፲፥፲፭–፲፮.