የብሉይ ኪዳን ነቢይ። ከይሁዳ ሀገር ውስጥ፣ ከሞሬሼትጌት ተወላጅ ነበር፣ እናም ሕዝቅያስ ንጉስ በነበረበት ጊዜ ተነበየ (ሚክ. ፩፥፩–፪)።
ከብሉይ ኪዳን መፅሐፎች ውስጥ መሲህ የሚወለድበት ከተማ ቤተልሔም እንደሆነ የሚገልጸው የሚክያስ መፅሐፍ ብቻ ነው (ሚክ. ፭፥፪)። በመፅሐፉ ውስጥ ጌታ ህዝቡን መከረ እናም ለእነርሱ ያደረገውን የበፊት በጎ ድርጊቱን ዘረዘረ፤ ከእነርሱም ፍትህ፣ ምህረት፣ እና ትሁትነትን ጠየቀ (ሚክ. ፮፥፰)።