ግድያ ደግሞም ቃየን; የሞት ቅጣት ተመልከቱ ሰውን ምክንያት ሳይኖረው ወይም በእቅድ መግደል። ግድያ ከመጀመሪያ ጊዜ ጀምሮ የተኮነነ ኃጢያት ነው (ዘፍጥ. ፬፥፩–፲፪፤ ሙሴ ፭፥፲፰–፵፩)። የሰውን ደም የሚያፈስስ ሁሉ ደሙ ይፈስሳል, ዘፍጥ. ፱፥፮ (ጆ.ስ.ት.፣ ዘፍጥ. ፱፥፲፪–፲፫; ዘፀአ. ፳፩፥፲፪; አልማ ፴፬፥፲፪). አትግደል, ዘፀአ. ፳፥፲፫ (ዘዳግ. ፭፥፲፯; ማቴ. ፭፥፳፩–፳፪; ሞዛያ ፲፫፥፳፩; ት. እና ቃ. ፶፱፥፮). ኢየሱስም፣ አትግደል አለ, ማቴ. ፲፱፥፲፰. ገዳዮች በሁለተኛው ሞት ክፍል አላቸው, ራዕ. ፳፩፥፰. እናንተ በልባችሁ ገዳዮች ናችሁ, ፩ ኔፊ ፲፯፥፵፬. እያወቀ ለሚገድል ለነፍሰ ገዳይ ወዮለት፣ ይሞታልና, ፪ ኔፊ ፱፥፴፭. ጌታ እግዚአብሔር ሰዎች መግደል እንደሌለባቸው አዝዞአል, ፪ ኔፊ ፳፮፥፴፪. መግደል በጌታ ፊት አስከፊ, አልማ ፴፱፥፭–፮. የሚገድል ይቅርታን አያገኝም, ት. እና ቃ. ፵፪፥፲፰. ከመካከላችሁ ማንም ሰው የሰውን ነፍስ ቢያጠፋ ወደምድሪቷ ሕግ አሳልፋችሁ ስጧቸው, ት. እና ቃ. ፵፪፥፸፱.