የጥናት እርዳታዎች
ሊቀ ካህን


ሊቀ ካህን

በክህነት ስልጣን ውስጥ አንዱ ሀላፊነት። ቅዱሣት መጻህፍት “ሊቀ ካህንን” በሁለት አስተያየት ይናገሩበታል፥ (፩) በመልከ ጼዴቅ ክህነት ውስጥ አንዱ ሀላፊነት፤ እና (፪) በሙሴ ህግ ስር፣ የአሮናዊ ክህነት አመራር ባለስልጣን።

የመጀመሪያው አስተያየት ኢየሱስ ክርስቶስ እንደ ታላቁ ሊቀ ካህን ያመለክታል። አዳም እና የአባት አለቆች ሁሉ ሊቀ ካህናት ነበሩ። ዛሬ፣ ሶስት ሊቀ ካህናት የቤተክርስቲያኗን አመራር ይመሰርታሉ እናም የሁሉም የክህነት ባለስልጣኖች እና የቤተክርስቲያን አባላት መሪዎች ናቸው። ዛሬ ቤተክርስቲያን ውስጥ ተጨማሪ ብቁ ወንዶች ትክክለኛ ሲሆኑ እንደ ሊቀ ካህናት ይሾማሉ። ሊቀ ካህናት በኤጲስ ቆጶሳት መጠራት፣ መለየት፣ እና መሾም አለባቸው(ት. እና ቃ. ፷፰፥፲፱፻፯፥፷፱–፸፩)።

በሁለተኛው አስተያየት፣ በሙሴ ህግ መሰረት፣ የአሮናዊ ክህነት አመራር ባለስልጣን ሊቀ ካህን ተብሎ ይጠራል። ይህ ስልጣን በዘር የሚወረስ እና በአሮን ቤተሰብ መካከል በበኩር በኩል የሚመጣ ነበር፣ አሮን እራሱም የአሮናዊ ስርዓት የመጀመሪያ ሊቀ ካህን ነበር (ዘፀአ. ፳፰–፳፱ዘሌዋ. ፰ት. እና ቃ. ፹፬፥፲፰)።