ስራዎች ጥሩም ይሁን መጥፎ፣ ሰው የሚፈጽመው። እያንዳንዱ ሰው በእራሱ ስራ ይፈረድበታል። ጌታ ለሰው ሁሉ እንደ ሥራው ይመልስለታል, ምሳ. ፳፬፥፲፪. መልካሙን ሥራችሁን እንዲያዩ ብርሃናችሁ እንዲሁ በሰው ፊት ይብራ, ማቴ. ፭፥፲፮ (፫ ኔፊ ፲፪፥፲፮). በሰማያት ያለውን የአባቴን ፈቃድ የሚያደርግ ወደ መንግስተ ሰማይ ይገባል, ማቴ. ፯፥፳፩. ከሥራ የተለየ እምነት የሞተ ነው, ያዕ. ፪፥፲፬–፳፮. በስራዎቻቸው ሊፈረድባቸው ይገባል, ፩ ኔፊ ፲፭፥፴፪ (ሞዛያ ፫፥፳፬). በጸጋ የምንድነው የምንችለውን ካደረግን በኋላ እንደሆነ እናውቃለን, ፪ ኔፊ ፳፭፥፳፫. ለመልካም ስራ በጭራሽ እንዳይታክቱ አስተምሯቸው, አልማ ፴፯፥፴፬. ሰዎች እንደስራቸው እንዲፈረድባቸው አስፈላጊ ነው, አልማ ፵፩፥፫. በሥራዎቻቸው ታውቁአቸዋላችሁ, ሞሮኒ ፯፥፭ (ት. እና ቃ. ፲፰፥፴፰). እኔ ጌታ ሁሉንም ሰዎች በስራዎቻቸው መሰረት እፈርድባቸዋለሁ, ት. እና ቃ. ፻፴፯፥፱.