እውቀት ደግሞም ማስተዋል; እውነት; ጥበብ ተመልከቱ በልዩም እንደሚያስተምረው ወይም እንደሚያረጋግጠው፣ እውነትን የማስተዋል እና የመረዳት ችሎታ። እግዚአብሔር አዋቂ ነው, ፩ ሳሙ. ፪፥፫. ጌታ በእውቀት ፍጹም ነው, ኢዮብ ፴፯፥፲፮. የጥበብ መጀመሪያ እግዚአብሔርን መፍራት ነው, ምሳ. ፩፥፯. ጥቂት ቃልን የሚናገር አዋቂ ነው, ምሳ. ፲፯፥፳፯. ምድር እግዚአብሔርን በማወቅ ትሞላለች, ኢሳ. ፲፩፥፱ (፪ ኔፊ ፳፩፥፱; ፴፥፲፭). እውቀትን መክፈቻ ወሰዳችሁ, ሉቃ. ፲፩፥፶፪. የክርስቶስን ፍቅር እውቀትን ያሳልፋል, ኤፌ. ፫፥፲፱. ትጋትን ሁሉ እያሳያችሁ በእምነታችሁ በጎነትን ጨምሩ, ፪ ጴጥ. ፩፥፭. ኔፊ የእግዚአብሔርን ቸርነት ታላቅ ዕውቀት ነበረው, ፩ ኔፊ ፩፥፩. መድኃኒታቸውንም ያውቃሉ, ፪ ኔፊ ፮፥፲፩. ጻድቃንም ጻድቅነታቸው ፍፁም እውቀት ይኖራቸዋል, ፪ ኔፊ ፱፥፲፬. መንፈስ እውቀት ይሰጣል, አልማ ፲፰፥፴፭. እውቀታችሁ በእዚያ ነገር ፍፁም ነው, አልማ ፴፪፥፴፬. ላማናውያን ወደ አዳኛቸው እውነታዊ እውቀት ይመጣሉ, ሔለ. ፲፭፥፲፫. ይህ ከእግዚአብሔር መሆኑን ፍፁም በሆነ ዕውቀት ታውቃላችሁ, ሞሮኒ ፯፥፲፭–፲፯. ቅዱሳን ታላቅ የእውቀት ሀብት ያገኛሉ, ት. እና ቃ. ፹፱፥፲፱. ንጹህ እውቀት ነፍስን በታላቅ ያሳድጋል, ት. እና ቃ. ፻፳፩፥፵፪. የቅዱስ የክህነት ቁልፎችን የያዘ እውቀቶችን ለማግኘት ችግር አይኖረውም, ት. እና ቃ. ፻፳፰፥፲፩. ሰው እውቀት በዚህ ህይወት ካገኘ፣ በሚመጣው አለም ውስጥ ተጨማሪ የተሻለ ሁኔታ ይኖረዋል, ት. እና ቃ. ፻፴፥፲፱. በደንቆሮነት ለመዳን ለሰው አስቸጋሪ ነው, ት. እና ቃ. ፻፴፩፥፮.