ሴም ደግሞም ኖኅ፣ የመፅሐፍ ቅዱስ የአባቶች አለቃ ተመልከቱ በብሉይ ኪዳን ውስጥ፣ የኖኅ ጻድቅ ወንድ ልጅ እና፣ በባህል መሰረት፣ አረብ፣ ዕብራውያን፣ ባቢሎናውያን፣ አሶር፣ እና ፎኒሲያውያን አባል የሆኑባቸው የሴማውያን ወይም የሴም ህዝብ ቅድም አባት (ዘፍጥ. ፭፥፳፱–፴፪፤ ፮፥፲፤ ፯፥፲፫፤ ፱፥፳፮፤ ፲፥፳፩–፴፪፤ ሙሴ ፰፥፲፪)። በኋለኛው ቀን ራዕይ ውስጥ ሴም “ታላቁ ሊቀ ካህን” ተብሎ ተጠቁሟል (ት. እና ቃ. ፻፴፰፥፵፩)።