ቡድን ደግሞም ክህነት ተመልከቱ ቡድን በሁለት መንገዶች ልንጠቀምባቸው እንችላለን፥ (፩) አንድ አይነት የክህነት ሀላፊነቶችን የያዙ ልዩ የሰዎች ቡድን። (፪) የቤተክርስቲያኗን ስራ በሚከናወንበት ስብሰባ ውስጥ ለመሳተፍ መገኘት የሚያስፈልጋቸው የክህነት ቡድን አብላጫው ወይም ዳግማዊ ቁጥር (ት. እና ቃ. ፻፯፥፳፰)። የቀዳሚ አመራር፣ የአስራሁለት ሀዋሪያት፣ እና የሰባዎች ቡድኖች እና እርስ በራስ ያላቸው ግንኙነት ተገልጸዋል, ት. እና ቃ. ፻፯፥፳፪–፳፮፣ ፴፫–፴፬ (ት. እና ቃ. ፻፳፬፥፻፳፮–፻፳፰). የእያንዳንዱ ቡድን በውሳኔው መስማማት አለባቸው, ት. እና ቃ. ፻፯፥፳፯. የእነዚህ ቡድኖች ውሳኔዎችም በሙሉ ጽድቅ ይሰራ, ት. እና ቃ. ፻፯፥፴–፴፪. የክህነት ቡድን ፕሬዘደንቶች ተገልጸዋል, ት. እና ቃ. ፻፯፥፹፭–፺፮. የሽማግሌዎች ቡድን የተመሰረተው ለማይጓዙ አገልጋዮች ነው, ት. እና ቃ. ፻፳፬፥፻፴፯.