ጓደኝነት ደግሞም አንድነት; ፍቅር ተመልከቱ ለኋለኛው ቀን ቅዱሳን፣ ማህበርተኛነት ጓደኝነትን፣ አገልግሎትን፣ ማነሳሳትን፣ እና ሌሎችን ማጠናከርን የሚያጠቃልል ነው። ባልንጀራህን እንደ ራስህ ውደድ, ዘሌዋ. ፲፱፥፲፰ (ማቴ. ፲፱፥፲፱; ት. እና ቃ. ፶፱፥፮). አንተም በተመለስህ ጊዜ ወንድሞችህን አጽና, ሉቃ. ፳፪፥፴፪. እርስ በርሳችሁ ፍቅር ቢኖራችሁ፥ ደቀ መዛሙርቴ ናችሁ, ዮሐ. ፲፫፥፴፭. ጠቦቶቼን ጠብቅ አለው, ዮሐ. ፳፩፥፲፭–፲፯. ለቅዱሳን በሆነው አገልግሎት እንዲተባበሩ ይህን ቸርነት በብዙ ልመና ከእኛ ይለምኑ ነበር, ፪ ቆሮ. ፰፥፩–፭. ኅብረታችንም ከአባት ጋር ከልጁም ጋር ነው, ፩ ዮሐ. ፩፥፫. ኔፋውያንና ላማናውያን እርስ በእርሳቸው ተባበሩ, ሔለ. ፮፥፫. እያንዳንዱ ሰው ወንድሙን እንደራሱ ይመልከት, ት. እና ቃ. ፴፰፥፳፬–፳፭. አንድ ካልሆናችሁ የእኔ አይደላችሁም, ት. እና ቃ. ፴፰፥፳፯. ጓደኛችሁና ወንድማችሁ ለመሆን ወደ ማህበርተኛነት እቀበላችኋለሁ, ት. እና ቃ. ፹፰፥፻፴፫.