ቅዱስ ደግሞም ቅድስና; ንጹህ፣ ንጹህነት ተመልከቱ ቅዱስ፣ አምላካዊ ጸባይ መኖር፣ ወይም መንፈሳዊ ወይም ስጋዊ ንጹህነት። የቅዱስ ተቃራኒም ተራ ወይም ተሳዳቢ ነው። እናንተም የካህናት መንግሥት የተቀደሰም ሕዝብ ትሆኑልኛላችሁ, ዘፀአ. ፲፱፥፭–፮ (፩ ጴጥ. ፪፥፱). ጌታ እስራኤልን እንዲህ አዘዘ፥ እኔ ቅዱስ ነኝና እናንተ ቅዱሳን ሁኑ, ዘሌዋ. ፲፩፥፵፬–፵፭. ንጹህ እጅ እና ንጹህ ልብ ያላቸው በእርሱ ቅዱስ ቦታ ይቆማሉ, መዝ. ፳፬፥፫–፬. በተቀደሰውና ባልተቀደሰው መካከል ይለዩ ዘንድ ሕዝቤን ያስተምሩ, ሕዝ. ፵፬፥፳፫. በቅዱስም አጠራር የጠራን እግዚአብሔር ነው, ፪ ጢሞ. ፩፥፰–፱. ከሕፃንነትህም ጀምረህ ቅዱሳን መጻሕፍትን አውቀሃል, ፪ ጢሞ. ፫፥፲፭. በእግዚአብሔር ተልከው ቅዱሳን ሰዎች በመንፈስ ቅዱስ ተነድተው ተናገሩ, ፪ ጴጥ. ፩፥፳፩. በእግዚአብሔር ውስጡ ባለው እውነትና ቅድስና መሰረት እንዲፈረድባቸው በፊቱ ይቆማሉ, ፪ ኔፊ ፪፥፲. ተፈጥሮአዊው ሰው በክርስቶስ የኃጢያት ክፍያ አማካኝነት ቅዱስ ሆነ, ሞዛያ ፫፥፲፱. በእግዚአብሔር ቅዱሱ ስርዓት ተራመዱ, አልማ ፯፥፳፪ (አልማ ፲፫፥፲፩–፲፪). ሶስት ደቀመዛሙርት በስጋ ተቀድሰው ቅዱስ ሆነዋል, ፫ ኔፊ ፳፰፥፩–፱፣ ፴፮–፴፱. በተቀደሱ ነገሮች አትቀልድ, ት. እና ቃ. ፮፥፲፪. ከእኔ ካልተሰጠ በስተቀረ ቅዱስ የሆነውን መጻፍ አትችልም, ት. እና ቃ. ፱፥፱. በቅድስና ለመሄድ ራሳችሁን ታስተሳስራላችሁ, ት. እና ቃ. ፵፫፥፱. ደቀ መዛሙርቴ በተቀደሰ ቦታ ላይ ይቆማሉ, ት. እና ቃ. ፵፭፥፴፪. ከላይ የሚመጣው ቅዱስ ነው, ት. እና ቃ. ፷፫፥፷፬. ትንሽ ልጆች የተቀደሱ ናቸው, ት. እና ቃ. ፸፬፥፯. ይህም ቅዱስ ይሆን ዘንድ ያን ቦታ እቀድሰዋለሁ, ት. እና ቃ. ፻፳፬፥፵፬. ጌታ ተመራጮችን ወደ ቅዱስ ከተማ ይሰበስባል, ሙሴ ፯፥፷፪.