አፖክርፋ ደግሞም መፅሐፍ ቅዱስ; ቅዱሳት መጻህፍት ተመልከቱ በእብራውያን መፅሐፍ ቅዱስ ውስጥ ያልተጨመሩት ነገር ግን በአንዳንድ የክርስትያን ቤተክርስትያናት ውስጥ የሚገኙት የአይሁድ ህዝቦች ቅዱሣት መጻህፍት። እነዚህ መጽሀፎች በብዙ ሁኔታዎች ብሉይ እና አዲስ ኪዳኖችን ለማያያዝ ጠቃሚ ናቸው እና በቤተክርስትያኗ ውስጥ እንደ ጠቃሚ ምንባብ አስተያየት ይሰጣቸዋል። አፖክርፋ በብዙ ጊዜ በትክክል የተተረጎሙ ናቸው ነገር ግን ትክክል ያልሆነ ጣልቃዎች ገብተውባቸዋል, ት. እና ቃ. ፺፩፥፩–፫. አፖክርፋ በመንፈስ የተብራሩትን ለመጠቀም ይችላል, ት. እና ቃ. ፺፩፥፬–፮.