የጥናት እርዳታዎች
እግዚአብሔር፣ አምላክ


እግዚአብሔር፣ አምላክ

በአምላክ ውስጥ ሶስት የተለያዩ ግለሰቦች አሉ፥ እግዚአብሔር፣ የዘለላለም አባት፤ ልጁ ኢየሱስ ክርስቶስ፣ እና መንፈስ ቅዱስ። በእያንዳንዱም እናምናለን (እ.አ. ፩፥፩)። ከኋለኛው ቀን ራዕይ አብና ወልድ ለመዳሰስ የሚቻል የስጋና የአጥንት ሰውነት እንዳላቸው እና መንፈስ ቅዱስ የስጋና የአጥንት ሰውነት የሌለው የመንፈስ ሰው እንደሆነ ተምረናል (ት. እና ቃ. ፻፴፥፳፪–፳፫)። እነዚህ ሶስት ሰዎች በፍጹም ህብረት እና በአላማና በትምህርት ስምምነት የተዋሀዱ ናቸው (ዮሐ. ፲፯፥፳፩–፳፫፪ ኔፊ ፴፩፥፳፩፫ ኔፊ ፲፩፥፳፯፣ ፴፮)።

እግዚአብሔር አብ

ይህም በአጠቃላይ በእግዚአብሔር ርዕስ የሚጠቀስ አብ፣ ወይም ኤሎኸም ነው። አብ ተብሎ የተጠራበት ምክንያት የመንፈሳችን አባት ስለሆነ ነው (ዘኁል. ፲፮፥፳፪፳፯፥፲፮ሚል. ፪፥፲ማቴ. ፮፥፱ኤፌ. ፬፥፮ዕብ. ፲፪፥፱)። እግዚአብሔር አብ የሁለንተና ታላቅ መሪ ነው። እርሱም ሀያል (ዘፍጥ. ፲፰፥፲፬አልማ ፳፮፥፴፭ት. እና ቃ. ፲፱፥፩–፫)፣ ሁሉን የሚያውቅ፣ (ማቴ. ፮፥፰፪ ኔፊ ፪፥፳፬) እናም በመንፈሱም በሁሉም ቦታ የሚገኝ ነው (መዝ. ፻፴፱፥፯–፲፪ት. እና ቃ. ፹፰፥፯–፲፫፣ ፵፩)። ሰውን ከተፈጠሩት ሌሎች ነገሮች ሁሉ የሚለየው ልዩ አይነት ግንኙነት በሰው ዘርና በእግዚአብሔር መካከል አለ፥ ወንዶች እና ሴቶች የእግዚአብሔር የመንፈስ ልጆች ናቸው (መዝ. ፹፪፥፮፩ ዮሐ. ፫፥፩–፫ት. እና ቃ. ፳፥፲፯–፲፰)።

አብ እግዚአብሔር ወደ ሰው መጥቶ የታየበት ወይም የተናገረበት የተመዘገቡ ጥቂት ጊዜዎች አሉ። ቅዱሣት መጻህፍት ከአዳም እና ከሔዋን ጋር ተነጋገረ (ሙሴ ፬፥፲፬–፴፩) እናም ኢየሱስን በተለያዩ ሁኔታዎች አስተዋወቀ ይላሉ (ማቴ. ፫፥፲፯፲፯፥፭ዮሐ. ፲፪፥፳፰–፳፱፫ ኔፊ ፲፩፥፫–፯)። በእስጢፋኖስ (የሐዋ. ፯፥፶፭–፶፮) እና በጆሴፍ ስሚዝ (ጆ.ስ.—ታ. ፩፥፲፯) ታየ። በኋላም ለጆሴፍ ስሚዝ እና ለስድኒ ሪግደን ታየ (ት. እና ቃ. ፸፮፥፳፣ ፳፫)። እግዚአብሔርን ለሚወዱና እራሳቸውን ለሚያጸዱ፣ እግዚአብሔር አንዳንዴ የማየትና ለእራሳቸው እግዚአብሔር እንደሆነ የማወቅ እድል ይሰጣል (ማቴ. ፭፥፰፫ ኔፊ ፲፪፥፰ት. እና ቃ. ፸፮፥፻፲፮–፻፲፰፺፫፥፩)።

እግዚአብሔር ወልድ

ያህዌህ ተብሎ የሚታወቀው አምላክ ወልድ፣ ኢየሱስ ክርስቶስ ነው (ኢሳ. ፲፪፥፪፵፫፥፲፩፵፱፥፳፮፩ ቆሮ. ፲፥፩–፬፩ ጢሞ. ፩፥፩ራዕ. ፩፥፰፪ ኔፊ ፳፪፥፪)። ኢየሱስ በአብ አመራር ስር ይሰራል እናም ከእርሱም ጋር በፍጹም ስምምነት ላይ ነው። የሰው ዘር በሙሉ የእርሱ ወንድሞችና እህቶች ናቸው፣ ምክንያቱም እርሱ ለኤሎኸም መንፈስ ልጆች ታላቅ ነውና። አንዳንድ ቅዱሣት መጻህፍት እርሱን እግዚአብሔር ብለው ይጠሩታል። ለምሳሌ፣ ቅዱሣት መጻህፍት “በመጀመሪያ እግዚአብሔር ሰማይንና ምድርን ፈጠረ” (ዘፍጥ. ፩፥፩) ይላል፣ ነገር ግን ፈጣሪው በእግዚአብሔር አብ አመራር ስር ኢየሱስ ነበር (ዮሐ. ፩፥፩–፫፣ ፲፣ ፲፬ዕብ. ፩፥፩–፪)።

እግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስ

መንፈስ ቅዱስም እግዚአብሔር ነው እናም ከሌሎች ስሞችና ርዕሶች መካከል፣ መንፈስ ቅዱስ፣ መንፈስ፣ እና የእግዚአብሔር መንፈስ ተብሎ ይጠራል። በመንፈስ ቅዱስ እርዳታ፣ ሰው የእግዚአብሔር አብን ፍላጎት ለማወቅ እና ኢየሱስ እርሱ ክርስቶስ እንደሆነ ለማወቅ ይችላል (፩ ቆሮ. ፲፪፥፫)።