ደማስቆ የሶርያ የጥንት ከተማ። ደማስቆ በበረሀ ዳርቻ የምትገኝ እናም በባራዳ ወንዝ በደንብ የምትጠጣ የለማች መሬት ናት። በቅዱሣት መጻህፍት ውስጥ በተደጋጋሚ የምትጠቀስ ናት (ዘፍጥ. ፲፬፥፲፭ ጀምሮ)። ከሞት የተነሳው ጌታ ለጳውሎስ ሲገለፅለት ወደ ደማስቆ እየተጓዘ ነበር (የሐዋ. ፱፥፩–፳፯፤ ፳፪፥፭–፲፮፤ ፳፮፥፲፪–፳)።