አይን፣ አይኖች በቅዱሣት መጻህፍት ውስጥ፣ አይን የእግዚአብሔርን ብርሀን ለመቀበል ሰው እንዳለው ችሎታ ምሳሌ በብዙ ጊዜ የሚጠቀሙበት ነው። በምሳሌም፣ የሰው አይን የመንፈሳዊ ጉዳይን እና የእግዚአብሔር ነገሮችን ማስተዋልን ያሳያል። የእግዚአብሔር ትእዛዝ ብሩህ ነው፥ ዓይንንም ያበራል, መዝ. ፲፱፥፰. ሰነፎች ዓይን እያላችሁ አታዩም, ኤር. ፭፥፳፩ (ማር. ፰፥፲፰). የሰውነት መብራት ዓይን ናት, ማቴ. ፮፥፳፪ (ሉቃ. ፲፩፥፴፬; ፫ ኔፊ ፲፫፥፳፪; ት. እና ቃ. ፹፰፥፷፯). የእናንተ ግን ዓይኖቻችሁ ስለሚያዩ ብፁዓን ናቸው, ማቴ. ፲፫፥፲፮. የማስተዋላችሁ አይኖች ብሩህ ይሆናሉ, ኤፌ. ፩፥፲፯–፲፰. በራሳቸው ዐይን ብልህና አስተዋይ ለሆኑት ወዮላቸው, ፪ ኔፊ ፲፭፥፳፩ (ኢሳ. ፭፥፳፩). የህዝቡም ዐይን እንዲከፈት፣ መፀለይ እናም መፆም ጀመሩ, ሞዛያ ፳፯፥፳፪. ሰይጣን አሳውሮአቸዋል, ፫ ኔፊ ፪፥፪. ለእግዚአብሔር ክብሩ በቀናነት ካላደረገ በስተቀር ማንም መፅሐፈ ሞርሞንን ለማምጣት ሀይል አይኖረውም, ሞር. ፰፥፲፭. ፲፪ በመንፈስ ሀይልም፣ አይኖቻችን ተከፈቱ እናም እውቀቶቻችንም ብሩህ ሆኑ, ት. እና ቃ. ፸፮፥፲፪. አይኖቻችሁን የሚያበራው ብርሀንም በእርሱ በኩል ነው, ት. እና ቃ. ፹፰፥፲፩. ለክብሬ ዐይናችሁ ቀና ብትሆን፣ ሰውነታችሁ ሁሉ ብሩህ ይሆናል, ት. እና ቃ. ፹፰፥፷፯.