ያዕቆብ፣ የይስሐቅ ልጅ ደግሞም ዔሳው; እስራኤል; ይስሐቅ ተመልከቱ የብሉይ ኪዳን የአባቶች አለቃና ነቢይ፤ የይስሀቅ እና የርብቃ መንታ ወንድ ልጆች ታናሹ (ዘፍጥ. ፳፭፥፲፱–፳፮)። ያዕቆብ ከወንድሙ ዔሳው በላይ በኩርን አገኘ። ይህም ያዕቆብ ብቁ ሆኖ እና በቃል ኪዳን ውስጥ ሲያገባ፣ ዔሳው በኩሩን በመጥላቱ እና ከቃል ኪዳን ውጪ በማግባቱ ምክንያት ነው (ዘፍጥ. ፳፭፥፴–፴፬፤ ፳፮፥፴፬–፴፭፤ ፳፯፤ ፳፰፥፮–፱፤ ዕብ. ፲፪፥፲፮)። ርብቃ ከጌታ ዔሳው ያዕቆብን እንደሚያገለግል ተማረች, ዘፍጥ. ፳፭፥፳፫. ከዔሳው በኩርነትን ገዛ, ዘፍጥ. ፳፭፥፳፱–፴፬. ወደ ሰማይ ስለሚደርስ መሰላል አለመ, ዘፍጥ. ፳፰. ያልን እና ራሔልን አገባ, ዘፍጥ. ፳፱፥፩–፴. አስራ ሁለት ወንድ ልጆች እና አንድ ሴት ልጅ ወለደ, ዘፍጥ. ፳፱፥፴፩–፴፥፳፬፤ ፴፭፥፲፮–፳. ባላን እና ዘለፋን አገባ, ዘፍጥ. ፴፥፫–፬፣ ፱. ስሙ ወደ እስራኤል ተቀየረ, ዘፍጥ. ፴፪፥፳፰. እግዚአብሔርን ፊት ለፊት አየ, ዘፍጥ. ፴፪፥፴. ዮሴፍን ከልጆቹ ሁሉ ይልቅ ይወደው ነበር, ዘፍጥ. ፴፯፥፫. ከቤተሰቡ ጋር ወደ ግብፅ ሄደ, ዘፍጥ. ፵፮፥፩–፯. ልጆቹን እና ዘሮቻቸውን ባረከ, ዘፍጥ. ፵፱. ሞተ, ዘፍጥ. ፵፱፥፴፫. ትእዛዛትን አከበረ፣ እናም ዛሬ ከአብርሐም እና ከይስሐቅ ጋር ወደ ዘለአለማዊነታቸው ገብተዋል፣ እና በዙፋናት ተቀምጠዋል, ት. እና ቃ. ፻፴፪፥፴፯.