ጭንቀት ደግሞም መገሰጽ፣ ተግሳጽ; መፅናት; መፈተን፣ ፈተና; ማሳደድ፣ መሳደድ ተመልከቱ በመከራ—በፈተናዎች፣ በችግርች፣ እና በጭንቀት—ሰው ወደ ጌታ በመሄድ ወደ መንፈሳዊ እድገት እና ዘለአለማዊ እርምጃ የሚመሩ ብዙ አጋጣሚዎች ሊኖረው ይችላል። እግዚአብሔር እራሱ ከመከራችሁና ከጭንቀታችሁ ሁሉ አድናችኋል, ፩ ሳሙ. ፲፥፲፱. በተጨነቁ ጊዜ ወደ እግዚአብሔር ጮኹ, መዝ. ፻፯፥፮፣ ፲፫፣ ፲፱፣ ፳፰. ጌታም የጭንቀት እንጀራን ቢሰጥህም አስተማሪህ እንግዲህ ከአንተ አይሰወርም, ኢሳ. ፴፥፳–፳፩. ለሁሉም ነገሮች ተቃራኒ መኖር አስፈላጊ ነው, ፪ ኔፊ ፪፥፲፩. መራራውን ካላወቁ ጣፋጩን ማወቅ አይችሉም, ት. እና ቃ. ፳፱፥፴፱. ጭንቀትህ ለትንሽ ጊዜም ቢሆን ነው, ት. እና ቃ. ፻፳፩፥፯–፰. እነዚህ ነገሮች ሁሉ ለአንተ ልምድ እንደሚሰጡህ እና ለአንተ ጥቅም እንደሆኑም እወቅ, ት. እና ቃ. ፻፳፪፥፭–፰. የጥሩውን ሽልማት እንዲያውቁ ዘንድ፣ መራራውን ይቀምሳሉ, ሙሴ ፮፥፶፭.