አዕምሮ የአዕምሮ ሀይል፤ የህሊና ሀሳብ ሀይሎች። በፍጹም ልብና በነፍስህ ፈቃድም አምልከው, ፩ ዜና ፳፰፥፱. ጌታ አምላክህን በፍጹም ነፍስህም ውደድ, ማቴ. ፳፪፥፴፯. ስለ ዓለም ማሰብ ሞት እንደሆነና፣ ስለመንፈሳዊ ነገር ማሰብ ዘለዓለማዊ ህይወት ነው, ፪ ኔፊ ፱፥፴፱. የጌታ ድምፅ በአዕምሮዬ መጣ, ኢኖስ ፩፥፲. ቃሉ ታላቅ ዝንባሌ ስላለው ከጎራዴ የበለጠ በአዕምሮአቸው ላይ ውጤት ይኖረዋል, አልማ ፴፩፥፭. በአዕምሮህ እነግርሃለሁ, ት. እና ቃ. ፰፥፪. በአእምሮህ ውስጥ ልታጠናው ይገባል, ት. እና ቃ. ፱፥፰. የዘለአለም ማስተዋልም በአዕምሮዎቻችሁ ላይ ይረፉ, ት. እና ቃ. ፵፫፥፴፬. ከዚህ በፊት አዕምሮአችሁ ጨልሞባችሁ ነበር, ት. እና ቃ. ፹፬፥፶፬. ወደ መኝታችሁ በጊዜ ሂዱ፤ ሰውነቶቻችሁ እና አዕምሮዎቻችሁ እንዲነቃቁ ዘንድ በማለዳም ተነሱ, ት. እና ቃ. ፹፰፥፻፳፬. ሰይጣን የእግዚአብሔርን ሀሳብ አያውቅም, ሙሴ ፬፥፮. እነርሱ አንድ ልብ እና አንድ አእምሮ ስለነበሩ፣ ጌታ ህዝቡን ፅዮን ብሎ ጠራቸው, ሙሴ ፯፥፲፰.