ኢዮርብዓም በብሉይ ኪዳን ውስጥ፣ ኢዮርብዓም የተከፋፈለችው እስራኤል የሰሜን ክፍል የመጀመሪያ ንጉስ ነበር። እርሱም የኤፍሬም ጎሳ አባል ነበር። ክፉው ኢዮርብዓም በይሁዳ ቤት እና በዳዊት ቤተሰብ ላይ አመጽን መራ። ኢዮርብዓም ለዳን እና ለቤቴል ህዝቦች ጣዖቶችን መሰረተ, ፩ ነገሥ. ፲፪፥፳፰–፳፱. አኪያ ኢዮርብዓምን ገሰጸው, ፩ ነገሥ. ፲፬፥፮–፲፮. በኢዮርብዓም መንገድ እስራኤልንም ባሳተበት ኃጢአት ይታወሳል, ፩ ነገሥ. ፲፭፥፴፬ (፩ ነገሥ. ፲፪፥፴).