የጥበብ ቃል
ለቅዱሳን ስጋዊ እና መንፈሳዊ ጥቅም ጌታ የገለጸው የጤንነት ህግ (ት. እና ቃ. ፹፱)። አሁን ይህም የጥበብ ቃል ተብሎ ይታወቃል። ጌታ ሁልጊዜም ተከታዮቹን የጤና መሰረታዊ መርሆችን ያስተምራል። ጌታ ለጆሴፍ ስሚዝ የትኛውን ምግብ መመገብ እንደሚገባ እና የትኛውን ምግብ ማስወገድ እንደሚገባ፣ እንዲሁም የጥበብ ቃልን ለሚያከብሩ ምድራዊ እና መንፈሳዊ በረከቶች ቃል ኪዳን በመግባት ገለጸ።