ልበ ሙሉነት ደግሞም መታመን; እምነት፣ ማመን ተመልከቱ በአንድ ነገር ላይ፣ በልዩም በአግዚአብሐእር ወይም በኢየሱስ ክርስቶስ ላይ፣ ማረጋገጫ፣ ማመን፣ ወይም እምነት መጣል። በሰው ከመታመን ይልቅ በእግዚአብሔር መታመን ይሻላል, መዝ. ፻፲፰፥፰. እግዚአብሔር መታመኛህ ይሆናልና, ምሳ. ፫፥፳፮. ክርስቶስ በሚገለጥበት ጊዜ፣ እምነት ይሆንልናል, ፩ ዮሐ. ፪፥፳፰. ክፉ ኔፋውያን የልጆቻቸውን መተማመን አጡ, ያዕቆ. ፪፥፴፭. ያሳምር፤ ከዚያም ልበ ሙሉነትህ በእግዚአብሔር ፊት እየጠነከረ ይሄዳል, ት. እና ቃ. ፻፳፩፥፵፭.