ተአምራት ደግሞም ምልክት; እምነት፣ ማመን ተመልከት በእግዚአብሔር ሀይል የተደረገ አስደናቂ ድርጊት። ታዕምራቶች በኢየሱስ ክርስቶስ ስራ ውስጥ አስፈላጊ የሆኑ ክፍሎች ናቸው። እነዚህም በተጨማሪ ፈውሶችን፣ ሙታንን ወደ ህይወት ዳግም መመለስ፣ እና ትንሳኤ ናቸው። ታዕምራቶች የኢየሱስ ክርስቶስ ወንጌል ክፍሎች ናቸው። ታዕምራቶች እንዲታዩ ዘንድ እምነት አስፈላጊ ነው (ማር. ፮፥፭–፮፤ ሞር. ፱፥፲–፳፤ ኤተር ፲፪፥፲፪)። ፈርዖን ሲናገር፣ ተአምራትን አሳዩኝ, ዘፀአ. ፯፥፱. በስሜ ተአምር ሠርቶ በቶሎ በእኔ ላይ ክፉ መናገር የሚችል ማንም የለም, ማር. ፱፥፴፱. ኢየሱስ የምልክቶች መጀመሪያ ቃና አደረገ, ዮሐ. ፪፥፲፩. እኔ የተአምራት አምላክ ነኝ, ፪ ኔፊ ፳፯፥፳፫. ድንቅ ስራን የሚሰራው በእግዚአብሔር ኃይል መሰረት ነው, አልማ ፳፫፥፮. ክርስቶስ በአሜሪካ ክፍለ አህጉር ውስጥ ለሚገኙት በነበራቸው ታላቅ እምነት ታላቅ ተአምራቶችን ለማሳየት ችሏል, ፫ ኔፊ ፲፱፥፴፭. እግዚአብሔር የተአምራት አምላክ መሆኑን አላቆመም, ሞር. ፱፥፲፭. እኔ ካላዘዝኳችሁ በስተቀር ተአምራትን አትፈልጉ, ት. እና ቃ. ፳፬፥፲፫–፲፬. ለአንዳንዶቹ ተአምራትን ማድረግ ተሰጥቷቸዋል, ት. እና ቃ. ፵፮፥፳፩ (ሞሮኒ ፲፥፲፪).