ልግስና ደግሞም ርህራሄ; በጎ ድርገት; አገልግሎት; ፍቅር ተመልከቱ የክርስቶስ ንጹህ ፍቅር (ሞሮኒ ፯፥፵፯)፤ ክርስቶስ ለሰው ልጆች ያለው እና የሰው ልጆች እርስ በራስ ሊኖራቸው የሚገባቸው ፍቅር (፪ ኔፊ ፳፮፥፴፤ ፴፫፥፯–፱፤ ኤተር ፲፪፥፴፫–፴፬)፤ መውደድ ብቻ ሳይሆን፣ ከሁሉም በላይ፣ ልዑላዊ፣ ጠንካራ አይነት የሆነ ፍቅር። እውቀት ያስታብያል ፍቅር ግን ያንጻል, ፩ ቆሮ. ፰፥፩. ንጹ ፍቅር የሆነው ልግስና ከሁሉም በላይ ምርጥ እና የበለጠ ነው, ፩ ቆሮ. ፲፫. የትእዛዝ ፍጻሜ ግን ከንጹሕ ልብ የሚወጣ ፍቅር ነው, ፩ ጢሞ. ፩፥፭. በወንድማማችም መዋደድ ፍቅርን ጨምሩ, ፪ ጴጥ. ፩፥፯. ጌታ ሰው ሁሉ ለጋስ መሆን እንዳለበት ትዕዛዝን ሰጥቷል, ፪ ኔፊ ፳፮፥፴ (ሞሮኒ ፯፥፵፬–፵፯). እምነት፣ ተስፋ፣ እና ልግስና ይኑራችሁ, አልማ ፯፥፳፬. ጌታ ለሰዎች ያለው ፍቅር ልግስና ነው, ኤተር ፲፪፥፴፫–፴፬. ሰዎች ልግስና ከሌላቸው በአባትህ መኖሪያ ያዘጋጀኸውን ስፍራ ሊወርሱ አይችሉም, ኤተር ፲፪፥፴፬ (ሞሮኒ ፲፥፳–፳፩). ሞሮኒ የሞርሞን እምነት፣ ተስፋ፣ እና ልግስና ቃላትን ጻፈ, ሞሮኒ ፯. ልግስና ሰዎችን ለጌታ ስራ ብቁ ያደርጋቸዋል, ት. እና ቃ. ፬፥፭–፮ (ት. እና ቃ. ፲፪፥፰). በልግስና ማሰሪያ ራሳችሁን አልብሱ, ት. እና ቃ. ፹፰፥፻፳፭. በልግስና ማሰሪያ ራሳችሁን አልብሱ, ት. እና ቃ. ፻፳፩፥፵፭.