መለኮታዊ ድጋፍን ለአንድ ሰው መስጠት። ለእውነተኛ ደስታ፣ ለደህንነት፣ ወይም ለብልፅግና ተጨማሪ ምክንያት የሚሆነው ማንኛውም ነገር በረከት ነው።
በረከቶች ሁሉ በዘለአለማዊ ህግጋት ላይ የተመሰረቱ ናቸው (ት. እና ቃ. ፻፴፥፳–፳፩)። እግዚአብሔር ልጆቹ በእዚህ ህይወት ደስታን እንዲያገኙ እልስሚፈልግ (፪ ኔፊ ፪፥፳፭)፣ ለትእዛዛቱ ታዛዥነታቸው ውጤታ (ት. እና ቃ. ፹፪፥፲)፣ ለጸሎት መልስ ወይም ለክህነት ስልጣን ስነስርዓት (ት. እና ቃ. ፲፱፥፴፰፤ ፻፯፥፷፭–፷፯)፣ ወይም በጸጋው በኩል (፪ ኔፊ ፳፭፥፳፫) በረከቶችን ይሰጣቸዋል።
ክርስቶስ ስለመባረክ የተናገራቸው አረፍት ነገሮች ታዋቂ የሆኑ ስለብሩክነት መግለጫ የተዘረዘረ ነው (ማቴ. ፭፥፩–፲፪፤ ፫ ኔፊ ፲፪፥፩–፲፪)።