ህይወት ደግሞም ብርሀን፣ የክርስቶስ ብርሀን; የዘለዓለም ህይወት ተመልከቱ በእግዚአብሔር ሀይል በኩል ሊሆን የቻለ ስጋዊና መንፈሳዊ አኗኗር። ዛሬ በፊትህ ሕይወትንና መልካምነትን፥ ሞትንና ክፋትን አኑሬአለሁ, ዘዳግ. ፴፥፲፭–፳. የሕይወትን መንገድ አሳየኸኝ, መዝ. ፲፮፥፲፩. ጽድቅንና ምሕረትን የሚከተል ሕይወትን ያገኛል, ምሳ. ፳፩፥፳፩. ነፍሱን የሚያገኝ ያጠፋታል፥ ነፍሱንም ስለ እኔ የሚያጠፋ ያገኛታል, ማቴ. ፲፥፴፱ (ማቴ. ፲፮፥፳፭; ማር. ፰፥፴፭; ሉቃ. ፱፥፳፬; ፲፯፥፴፫). የሰው ልጅ የሰውን ነፍስ ሊያድን እንጂ ሊያጠፋ አልመጣም, ሉቃ. ፱፥፶፮. በእርሱ ሕይወት ነበረች፥ ሕይወትም የሰው ብርሃን ነበረች, ዮሐ. ፩፥፬. በእርሱ የሚያምን ከሞትም ወደ ሕይወት ይሻገራል እንጂ ወደ ፍርድ አይመጣም, ዮሐ. ፭፥፳፬. እኔ መንገድና እውነት ሕይወትም ነኝ, ዮሐ. ፲፬፥፮. በዚች ሕይወት ብቻ ክርስቶስን ተስፋ ያደረግን ከሆነ፣ ከሰው ሁሉ ይልቅ ምስኪኖች ነን, ፩ ቆሮ. ፲፭፥፲፱–፳፪. እግዚአብሔርን መምሰል ግን የአሁንና የሚመጣውን ሕይወት ተስፋ አለው, ፩ ጢሞ. ፬፥፰. ልጆቻችን በክርስቶስ የሆነውን ህይወት ወደፊት ይመልከቱ, ፪ ኔፊ ፳፭፥፳፫–፳፯. ይህ ጊዜ ለሰዎች እግዚአብሔርን ለመገናኘት የዝግጅት ወቅት ነው, አልማ ፴፬፥፴፪ (አልማ ፲፪፥፳፬). እኔ የአለም ብርሃን እናም ህይወት ነኝ, ፫ ኔፊ ፱፥፲፰ (ሞዛያ ፲፮፥፱; ፫ ኔፊ ፲፩፥፲፩; ኤተር ፬፥፲፪). በህይወትም ይሁን በሞት፣ ታማኝ የሆኑት የተባረኩ ናቸው, ት. እና ቃ. ፶፥፭. እግዚአብሔርንና የላከውን ኢየሱስ ክርስቶስን ያውቁ ዘንድ ይህች የዘላለም ሕይወት ናት, ት. እና ቃ. ፻፴፪፥፳፬. የሰውን ህያውነት እና ዘለአለማዊ ህይወት አምጥቶም የማሳለፍ ስራዬ እና ክብሬ ይህም ነው, ሙሴ ፩፥፴፱.