እድፍ፣ እድፍነት ደግሞም ኃጢያተኛ፣ አመፃ; ኃጢያት; ንጹህ እና ርኩስ; እግዚአብሔርን የሚጠላ; ክፉ፣ ክፋት ተመልከቱ ለእግዚአብሔር በፈቃደኝነት ታዛዥ ባለመሆን ምክንያት መንፈሳዊ ርኩስነት። ጌታም የጽዮንን ቈነጃጅት እድፍ ያጥባል, ኢሳ. ፬፥፬ (፪ ኔፊ ፲፬፥፬). የእግዚአብሔር መንግስት የረከሰ አይደለም, ፩ ኔፊ ፲፭፥፴፬ (አልማ ፯፥፳፩). የረከሱትም አሁንም ርኩሳን ይሆናሉ, ፪ ኔፊ ፱፥፲፮ (ሞር. ፱፥፲፬). ልብሳችሁ በቆሻሻ ተበክሎ በእግዚአብሔር የፍርድ ወንበር ፊት የምትቆሙ ከሆነ ማንኛችሁም ምን ይሰማችኋል, አልማ ፭፥፳፪. የረከሱት ረክሰው መቅረት አለባቸው, ት. እና ቃ. ፹፰፥፴፭. መቼ አርፋለሁ፣ እና ከእኔ ውስጥ ከወጡት እድፍ እነጻለሁን, ሙሴ ፯፥፵፰.