ባርነት ደግሞም ነጻ፣ ነጻነት ተመልከቱ በስጋ ወይም በመንፈስ መታሰር የእስራኤል ቤት በኃጢአታቸው ምክንያት ተማረኩ, ሕዝ. ፴፱፥፳፫. ይማረክ ዘንድ ያለው ማንም ቢኖር ወደ ምርኮነት ይሄዳል, ራዕ. ፲፫፥፲. ክፉዎች ወደ ዲያብሎስ ምርኮ ይሰጣሉ, ፩ ኔፊ ፲፬፥፬፣ ፯. ሰዎች ነፃነትን ወይም ዘለዓለማዊ ህይወትን ለመምረጥ ነጻነት አላቸው, ፪ ኔፊ ፪፥፳፯. የስጋ ፈቃድ ለዲያብሎስ መንፈስ የምርኮ ሀይል ይሰጣል, ፪ ኔፊ ፪፥፳፱. የአባቶቻችሁን በምርኮ መቆየት በሚገባ ታስታውሳላችሁን, አልማ ፭፥፭–፮. ልባቸውን የሚያጠጥሩ በዲያብሎስ ምርኮ ይወሰዳሉ, አልማ ፲፪፥፲፩. ዘወትር ንቁ መሆን እና መፀለይ አለባችሁ፤ አለበለዚያ በዲያብሎስ ትፈተናላችሁ እናም የእርሱ ምርኮኛም ትሆናላችሁ, ፫ ኔፊ ፲፰፥፲፭.