የጥናት እርዳታዎች
አብድዩ


አብድዩ

ስለኤዶም መጥፋት አስቀድሞ የተናገረ የብሉይ ኪዳን ነቢይ። የተነበየው ምናልባት ኢዮራም በነገሰበት ጊዜ (፰፻፵፰–፰፻፵፬ ም.ዓ.) ወይም በ፭፻፹፮ ም.ዓ. ውስጥ ባቢሎን በወረረችበት ጊዜ ነበር።

ትንቢተ አብድዩ

የብሉይ ኪዳን መፅሐፍ። አንድ ምዕራፍ ብቻ ነበረው። በውስጡም፣ አብድዩ ስለኤዶም መጥፋት ጻፈ እናም በፅዮን ተራራ ላይ አዳኞች እንደሚቆሙ ተነበየ።