ስጋ ደግሞም ሰውነት; ስጋዊ; ስጋዊ፣ የሚሞት; ፍጥረታዊ ሰው ተመልከቱ ስጋ የተለያዩ ትርጉሞች አሉት፥ (፩) የሰው ዘርን፣ የእንስሳትን፣ የወፎችን፣ ወይም የአሳዎችን ሰውነቶች የሚሸፍን የሰውነት መሰሪያ፤ (፪) ሟችነት፤ ወይም (፫) ስጋዊ የፍጥረታዊ ሰው። የሰውነት መሰሪያ ሕይወት ያለው ተንቀሳቃሽ ሁሉ መብል ይሁናችሁ, ዘፍጥ. ፱፥፫. አስፈላጊ ሳይሆን እንስሳት አይገደሉ, ጆ.ስ.ት.፣ ዘፍጥ. ፱፥፲–፲፩ (ት. እና ቃ. ፵፱፥፳፩). እንስሳትን እና ወፎችን ለሰው ምግብ እና ለልብስ የሚጠቀምባቸው ናቸው, ት. እና ቃ. ፵፱፥፲፰–፲፱ (ት. እና ቃ. ፶፱፥፲፮–፳). ስጋን በቁጠባ እንጠቀምባቸው, ት. እና ቃ. ፹፱፥፲፪–፲፭. ሟችነት ኢየሱስ ወደ ሟችነት የተወለደው የአብ አንድያ ልጅ ብቻ ነው, ዮሐ. ፩፥፲፬ (ሞዛያ ፲፭፥፩–፫). አዳም የመጀመሪያም ስጋ ሆነ, ሙሴ ፫፥፯. ስጋዊ ፍጥረታዊ ሰው ሥጋ ለባሹንም ክንዱ የሚያደርግ ሰው ርጉም ነው, ኤር. ፲፯፥፭. መንፈስ ተዘጋጅታለች፥ ሥጋ ግን ደካማ ነው, ማር. ፲፬፥፴፰. የሥጋ ምኞት ከአባት አይደለም, ፩ ዮሐ. ፪፥፲፮. ኔፊ በስጋውና በኃጢያቶች ምክንያት አዘነ, ፪ ኔፊ ፬፥፲፯–፲፰፣ ፴፬. ከዲያብሎስና ከስጋ ፈቃድጋር አታስታርቁ, ፪ ኔፊ ፲፥፳፬.