ካስማ
ከኋለኛው ቀን ቅዱሳን የኢየሱስ ክርስቶስ ቤተክርስቲያን ድርጅቶች እና ማስተዳደሪያ ክፍል አንዱ። ካስማ በብዙ ዎርዶች ወይም ቅርንጫፎች የተሰራ ነው። በኢሳይያስ ፶፬፥፪ ውስጥ “አውታሮችሽን አስረዝሚ ካስሞችሽንም አጽኚ” በማለት የድንኳን ምስልን እንደገለጸው፣ ይህም የተመደበ የቦታዎች ገደብ ያለው ነው። ካስማ ለተበተኑት እስራኤል ቅሪዎች መሰብሰቢያ ቦታ ነው (ት. እና ቃ. ፹፪፥፲፫–፲፬፤ ፻፩፥፲፯–፳፩)።