አለም ደግሞም ምድር; ስጋዊ፣ የሚሞት; ባቢሎን ተመልከቱ ምድር፤ ስጋዊ ሰው የሚፈተንበት ቦታ። በምሳሌም፣ የእግዚአብሔርን ትእዛዛት የማያከብሩ ሰዎች። ምድራዊ ህይወት በዓለም ሳላችሁ መከራ አለባችሁ, ዮሐ. ፲፮፥፴፫. እስከሞትም አትፍሩ፤ በዚህ አለም ደስታችሁ ሙሉ አይደለምና, ት. እና ቃ. ፻፩፥፴፮. ትእዛዛትን የማያከብሩ ሰዎች ዓለሙን ስለ ክፋታቸው እቀጣለሁ, ኢሳ. ፲፫፥፲፩ (፪ ኔፊ ፳፫፥፲፩). ዓለም ቢጠላችሁ ከእናንተ በፊት እኔን እንደ ጠላኝ እወቁ, ዮሐ. ፲፭፥፲፰–፲፱. ትልቁና ሰፊው ህንፃ የዓለም ኩራት ነው, ፩ ኔፊ ፲፩፥፴፮. አለም በሃጢያት እየበሰለ ነው, ት. እና ቃ. ፲፰፥፮. ከአለም ነገሮች ራስህን ንጹህ እና ነውር የሌለበት አድርግ, ት. እና ቃ. ፶፱፥፱. ታማኝ የሆነው እና የሚጸናውም አለምን ያሸንፋል, ት. እና ቃ. ፷፫፥፵፯. በአለም አይነት ኑሮ መኖር አይገባችሁም, ት. እና ቃ. ፺፭፥፲፫. የአለም መጨረሻ አዲስ አዲስ ምድር እፈጥራለሁ፣ የቀደሙትም አይታሰቡም, ኢሳ. ፷፭፥፲፯ (ራዕ. ፳፩፥፩; እ.አ. ፩፥፲). እንክርዳድ ተለቅሞ በእሳት እንደሚቃጠል፥ በዓለም መጨረሻ እንዲሁ ይሆናል, ማቴ. ፲፫፥፵፣ ፵፱ (ሚል. ፬፥፩; ያዕቆ. ፮፥፫). የወይኑን ስፍራዬን በእሳት እንዲቃጠል አደርገዋለሁ, ያዕቆ. ፭፥፸፯ (ት. እና ቃ. ፷፬፥፳፫–፳፬). ጌታ ሰይጣንን እና ስራዎቹን በአለም መጨረሻ ያጠፋል, ት. እና ቃ. ፲፱፥፫. ምድር ብትሞትም፣ እንደገናም ህይወት ይሰጣታል, ት. እና ቃ. ፹፰፥፳፭–፳፮. ጌታም ለሔኖክ እስከ አለም መጨረሻ ድረስ አሳየው, ሙሴ ፯፥፷፯.