የእግዚአብሔር በግ ደግሞም ኢየሱስ ክርስቶስ; የኃጢያት ዋጋን መክፈል፣ የኃጢያት ክፍያ; ፋሲካ ተመልከቱ ኢየሱስን ለእኛ ጥቅም እንደሚሰዋው የሚያመለክተው ለአዳኝ የተሰጠ ስም። ለመታረድ እንደሚነዳ ጠቦት መጥቷል, ኢሳ. ፶፫፥፯ (ሞዛያ ፲፬፥፯). እነሆ የዓለምን ኃጢአት የሚያስወግድ የእግዚአብሔር በግ, ዮሐ. ፩፥፳፱ (አልማ ፯፥፲፬). እድፍ እንደ ሌለው እንደ በግ ደም በክቡር የክርስቶስ ደም እንደ ተዋጃችሁ ታውቃላችሁ, ፩ ጴጥ. ፩፥፲፰–፳. የታረደው በግ ክብር ሊቀበል ይገባዋል, ራዕ. ፭፥፲፪. በበጉ ደም የተነሣ በሰይጣን ላይ ድል ነሳን, ራዕ. ፲፪፥፲፩. እነዚህ በእርሱ ባላቸው እምነት ምክንያት በበጉ ደም ነፅተዋል, ፩ ኔፊ ፲፪፥፲፩. የእግዚአብሔርም በግ የዘለአለማዊው አባት ልጅና የአለም አዳኝ ነው, ፩ ኔፊ ፲፫፥፵ (፩ ኔፊ ፲፩፥፳፩). ምናልባት በመጨረሻው እና በዚያ በታላቁ ቀን እንከን የሌላችሁ፣ ንፁህ፣ መልካም፣ እናም በበጉ ደም የፀዳችሁ ሆናችሁ ትገኙ ዘንድ ወደ አብ በኢየሱስ ስም በኃይል ጩሁ, ሞር. ፱፥፮ (ራዕ. ፯፥፲፬; አልማ ፴፬፥፴፮). ፵፯ የሰው ልጅ ከምድር መሰረት ጀምሮም የተገደለው በግ ነው, ሙሴ ፯፥፵፯.